የወላሽማ ስርወ መንግስት Walashma dynasty

የዋላሽማ ስርወ መንግስት በኢፋት (በአሁኑ ምስራቅ ሸዋ ) የተመሰረተ የአፍሪካ ቀንድ የመካከለኛው ዘመን የሙስሊም ስርወ መንግስት ነበር። በ13ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የተመሰረተው የዛሬይቱ ሶማሊያ፣ ጅቡቲ እና ምስራቃዊ የኢትዮጵያ ክፍል ውስጥ የኢፋት እና አዳል ሱልጣኔቶችን አስተዳድሯል።

የዘር ሐረግ

የኢፋት እና የአደል የዋሽማ መሳፍንት የአረብ የዘር ሐረግ ወጎች እንዳላቸው ይናገራሉ። በዘር ሀረግ የዋሽማ ወጎች ከባኑ መክዙም ጎሳ በኤል መቅሪሲ የተወሰደ ነው። ግን የኢፋት ሱልጣኔት የዘር ሐረግ የከሊፋው አሊ እና የጃፋር ኢብኑ አቢ ጧሊብ ወንድም ከሆነው አቂል ብን አቢ ጣሊብ ነው። የኋለኛው በሀርላ ክልል ውስጥ ከሰፈሩት ቀደምት ሙስሊሞች መካከል አንዱ ነበር። ነገር ግን የዋላስማ ከፊል አፈ ታሪክ እንደሚያረጋግጠው ዑመር ኢብኑ-ዱንያ-ሃውዝ እንደ ቅድመ አያት ኸሊፋ የዓልይ ልጅ አል-ሐሰን ነበር። ይህ በሁለቱም መቅሪዚ አይደገፍም።እና የዋሽማ ዜና መዋዕል። ነገር ግን ሁለቱም የስርወ መንግስት መስራች እንደነበሩ የሚናገሩት ዑመር ኢብኑ-ዱንያ-ሃውዝ የቁረይሽ ወይም የበኑ ሃሺም ተወላጆች ነበሩ። የአስራ አራተኛው ክፍለ ዘመን አረብ የታሪክ ምሁር ኢብን ካልዱን የዋላስማ ቅድመ አያቶች በአንድ ወቅት የዳሞት መንግስት ገባር እንደነበሩ ይጠቅሳሉ።

ይሁን እንጂ አብዛኞቹ የታሪክ ተመራማሪዎች የዋላሽማ ሥርወ መንግሥት የአካባቢው ተወላጆች እንደሆኑ አድርገው ይመለከቱታል። ኤንሪኮ ችሩሊ እና ጄ.ስፔንሰር ትሪሚንግሃም እንደ አርጎባዎች ጎሳ አድርገው ይቆጥሯቸዋል። ዋላስማ በታሪክ ከአርጎባ የዶባ ህዝብ ቅድመ አያቶች ጋር የተሳሰረ ነው። የሀረሪ ህዝብም ከዋልስማ ጋር ተቆራኝተናል ይላሉ። ባህሩ ዘውዴ፣ ሪቻርድ ፓንክረስት ፣ ዲጂብሪል ኒያን እና ሌሎችም የዋላስማ ሱልጣኖች የኢፋት እና የአደል አብላጫ የአርጎባ እና ሀረሪ እንደሆኑ አድርገው ይመለከቱታል። ኤንሪኮ ችሩሊ ከኡመር ኢብኑ ዱንያሁዝ ቅድመ አያቶች አንዱ የ10ኛው ክፍለ ዘመን የሶማሊያዊ " አው " ባርካድሌ ከአረብ ነው። ጄ.ስፔንሰር ትሪሚንግሃም ይህ የማይመስል ነገር እንደሆነ ይቆጥረዋል፣ ምክንያቱም በአካባቢው ወግ መሰረት ከ500 ዓመታት በላይ የኖረ እና በ16ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ ስለሞተ የሚል ምክኒያት አስቀምጧል።

የኢፋት የዋላስማ ስርወ መንግስት ከአዳል መሪዎች ጋር ተከታታይ የጋብቻ ጥምረት እንደጀመረ በአረብ ፋቂህ “የአቢሲኒያ ወረራ” ዜና መዋዕል እንደገለጸው በመጨረሻው የኢፋት ሰአድ አድ-ዲን II የዋላስማ ገዥ የተወለዱ የሃርላ ጌቶች በአስራ ስድስተኛው ክፍለ ዘመን የኢትዮጵያ-አዳል ጦርነት ተሳትፈዋል። በአዳል የመጨረሻው የታወቀው የዋልስማ አባል በአስራ ስድስተኛው ክፍለ ዘመን የሐረር ሰው ባራካት ኢብን ኡመር ዲን ነው። የሐርላ ካቢርቶ እንዲሁም ከዋላስማ ሥርወ መንግሥት የመነጨው ዶባ በ1769 በሙዳይቶ ሥርወ መንግሥት ተገለበጡ። የአፋር በአውሳ (በአሁኑ አፋር ክልል ) የከቢርቶ ሼክ ከቢር ሀምዛ ዘር በብራና ጽሑፎች ታሪካቸውን ጠብቀዋል።

ዋላስማ የሚለው የማዕረግ ስም አሁንም በኢፋት ግዛት እስከ አስራ ዘጠነኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ ድረስ የዚያ ክልል ገዥዎች ከአሮጌው ስርወ መንግስት ተወላጆች ነን በሚሉ ሰዎች ይገለገሉበት ነበር። በ1993ዓ.ም መሐመድ ሳሌህ ቅድመ አያቶቻቸው እንደሆኑ የተናገረዉ የኢፋት አርጎባ ዋላስማ ቅድመ አያቶቹ ለዘመናት የሸዋ-ሀረር መንገድ ነጋዴዎች እንደነበሩ ገለፀ።

ቋንቋ

የታሪክ ተመራማሪዎች እንደሚናገሩት የአደል ህዝብ እንዲሁም ገዥዎቹ ኢማሞች እና ሱልጣኖች የሚናገሩት ቋንቋ የወቅቱን የሀረሪ ቋንቋ ይመስላል። እሱም የይፋትና አደል ሱልጣኖች ቋንቋ ለአረብኛ ቅርበት ያለው የአርጎብኛ ቋንቋ ነው። አርጎብኛ ቋንቋ ከደቡብ ሴማዊ ቋንቋ አንዱ ነው። የ19ኛው ክፍለ ዘመን ኢትዮጵያዊት የታሪክ ምሁር አስማ ጊዮርጊስ ራሳቸው ዋላስማ አረብኛ ይናገሩ እንደነበር ይጠቁማሉ።

የኢፋት ሱልጣኔት (1285–1415እኤአ)

ዋና መጣጥፍ፡ የኢፋትየወላሽማ ስርወ መንግስት

በ13ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ ላይ ሰሜናዊ ሀረርጌ በማክዙሚ ስርወ መንግስት ስር የተሰየመ የሙስሊም ሱልጣኔት መቀመጫ ነበረች። ሱልጣኔቱ በውስጥ ሽኩቻ እየተበጣጠሰ እና ከአጎራባች ሙስሊም መንግስታት ጋር በተደረገው ትግል መዳከሙን የወቅቱ ምንጭ ይገልፃል። በ1278 ከነዚህ አጎራባች ግዛቶች አንዱ በምስራቅ ሸዋ ኢፋት የሚባል በዋላሽማ መሪነት የሸዋ ሱልጣኔትን ወረረ። ከጥቂት አመታት ትግል በኋላ ሱልጣኔቱ ወደ ኢፋት ተጠቃሏል ። ይህ ቁርኝት ብዙውን ጊዜ በዑመር (ረዐ) ነው የሚነገረው ነገር ግን ሸዋ በተቀላቀለበት ጊዜ 50 ዓመታትን አስቆጥሯል። ምናልባትም የልጅ ልጁ ጀማል አድ-ዲን ወይም ምናልባትም የልጅ የልጅ ልጁ አቡድ ሊሆን ይችላል። በ1288 ሱልጣን ዋሊ አስማ ሁባትን በተሳካ ሁኔታ ድል አደረገ። አዳል እና ሌሎች በክልሉ ውስጥ ያሉ ሙስሊም መንግስታት። ኢፋትን በአፍሪካ ቀንድ ውስጥ ካሉት የሙስሊም መንግስታት ሁሉ የላቀ ኃያል መንግሥት ማድረግ።

በ1332 የኢፋት ሱልጣን ቀዳማዊ ሃቅ አድ-ዲን በአቢሲኒያ አፄ አምዳ ስዮን ወታደሮች ላይ በወታደራዊ ዘመቻ ተገደለ ። አምዳ ስዮን በመቀጠል ጀማል አድ-ዲንን አዲሱን ንጉስ አድርጎ ሾመ፣ በመቀጠልም የጀማል አድ-ዲን ወንድም ናስር አድ-ዲን ሾመ ። ይህ ውድቀት ቢሆንም የኢፋት ሙስሊም ገዥዎች ዘመቻቸውን ቀጥለዋል። አቢሲኒያው ንጉሠ ነገሥት በአካባቢው ያሉትን ሙስሊሞች “የጌታ ጠላቶች” ብሎ ፈርጀው ነበር፣ አሁንም በ15ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ ኢፋትን ወረረ። ከብዙ ተጋድሎ በኋላ የኢፋት ጦር ተሸንፎ የሱልጣኔቱ ገዥ የነበረው ንጉስ ሰአድ አድ-ዲን 2ኛ ወደ ዘይላ ሸሸ። እዚያም በአቢሲኒያ ጦር ተከትለው ገደሉት:የይፋት ስርወ መንግስት አከተመ።

የይፋት የወላስማ ሱልጣኖች ዝርዝር
ተቁ ገዥ ስም አባት ስም
1 ኡመር ወላስማ
2 አሊ "ባዚኡ" አመር
3 ሐቀዲን ኡመር
4 ሁሴን ኡመር
5 ናስር አዲን ኡመር
6 መንሱር ኡመር

የይፋት ወላስማ ሱልጣኖች ለማስተካከል

Ruler Name/

የመሪው ስም

Reign/የአስተዳደሩበት ዘመን ማስታወሻ
1 ሱልጣን ዑመር ዱኒያሁዝ 1185 - 1228 የዋላስማ ሥርወ መንግሥት መስራች፣ ቅፅል ስሙ አዱንዮ ወይም ዊሊንውሊ ነበር።
2 ሱልጣን ʿአሊ "ባዚኡ" ኡመር 1228 - 12?? የዑመር ዱንያሁዝ ልጅ
3 ሱልጣን ሐቀዲን ኡመር 12?? - 12?? የዑመር ዱንያሁዝ ልጅ
4 ሱልጣን ሁሴይን ʿዑመር 12?? - 12?? የዑመር ዱንያሁዝ ልጅ
5 ሱልጣን ናስረዲን ʿዑመር 12?? - 12?? የዑመር ዱንያሁዝ ልጅ
6 ሱልጣን መንሱር ʿአሊ 12?? - 12?? የዓሊ ልጅ “ባዚዊ” ዑመር
7 ሱልጣን ጀማልአድዲን ʿአሊ 12?? - 12?? የዓሊ ልጅ “ባዚዊ” ዑመር
8 ሱልጣን አቡድ ጀማልአዲን 12?? - 12?? የጀማልአድዲን ʿአሊ ልጅ
9 ሱልጣን ዙቤር አቡድ 12?? - 13?? የአቡድ ጀማልአድዲን ልጅ
10 ሚይቲ ለይላ አቡድ 13?? - 13?? የአቡድ ጀማልዲን ሴት ልጅ
11 Sulṭān ḤaqqudDīn Naḥwi 13?? - 1328 Son of Naḥwi Mansur, grandson of Mansur ʿUmar
12 Sulṭān SabiradDīn Maḥamed "Waqōyi" Naḥwi 1328 - 1332 Son of Naḥwi Mansur, defeated by Emperor Amde Seyon of Abyssinia, who replaced him with his brother JamaladDīn as a vassal.
13 Sulṭān JamaladDīn Naḥwi 1332 - 13?? Son of Naḥwi Mansur, vassal king under Amde Seyon
14 Sulṭān NasradDīn Naḥwi 13?? - 13?? Son of Naḥwi Mansur, vassal king under Amde Seyon
15 Sulṭān "Qāt" ʿAli SabiradDīn Maḥamed 13?? - 13?? Son of SabiradDīn Maḥamed Naḥwi, rebelled against Emperor Newaya Krestos after the death of Amde Seyon, but the rebellion failed and he was replaced with his brother Aḥmed
16 Sulṭān Aḥmed "Harbi Arʿēd" ʿAli 13?? - 13?? Son of ʿAli SabiradDīn Maḥamed, accepted the role of vassal and did not continue to rebel against Newaya Krestos, and is subsequently regarded very poorly by Muslim historians
17 Sulṭān Ḥaqquddīn Aḥmed 13?? - 1374 Son of Aḥmed ʿAli
18 Sulṭān SaʿadadDīn Aḥmed 1374 - 1403 Son of Aḥmed ʿAli, killed in the Abyssinian invasion of Ifat under Dawit I or Yeshaq I[1]

የአዳል ሱልጣኔት (1415–1559እኤአ)

የአዳል ሱልጣኔት ተብሎ ይታወቅ የነበረው ግዛት በመካከለኛው ዘመን (ከ1415 - 1555 እኤአ.) የነበረ የብዙ እስልምና ተከታይ ጎሳዎች ድብልቅ የነበረ ግዛት ነው። አንዳንድ ተመራማሪወች አብዛኛው አዳል የአፋር ጎሳዎች ተዋጾ ነበረበት ሲሉ አንዳንዶች ደግሞ ባብዛኛው ከዲር እና ዳሩድ የሶማሌ ነገዶች የተውጣጣ ነበር ይላሉ። የአዳልን ሱልጣኔት አብዛኛ ጎሳ ስብጥር ክርክር ይውደቅ እንጂ በርግጥም ሱልጥኔቱ የብዙ ጎሳዎች ስብስብ እንደነበር ግን ክርክር የለም። .የሱልጣኖቹ የዘር ሃረግ የሰአድ አዲን አህመድ አሊ ልጆች የተመሰረተ ነው።

የአዳል ሱልጣኔት

ስለ አዳል ሱልጣኔት በትንሹ (ከ1415- 1577 ዓ.ል.)

በአብዱ እንድሪስ (ከሚሴ)

አስራ ሁለተኛው የኢትዮጵያ ሰለሞናዊ ነጋሲ የነበረው ወጣቱ አጼ ዳዊት በ1413 ዓ.ል. በአጠገቡ በነበረው የኢፋት ሱልጣኔት ላይ ሀይለኛ ጥቃት ከፈተ። የሱልጣኔቱ ገዠ የነበረውን ሱልጣን ሰዓደዲንን በዜይላ ከተማ ከገደለው በኋላም ኢፋትን ከአጼው ግዛተ መንግስት ጋር ቀላቀለው። ሆኖም አጼ ዳዊት በቁጥጥር ስር ካዋለው የኢፋት ግዛት በሙሉ ሀይሉ ለመግዛት የቻለው ከአዋሽ ወንዝ በስተምዕራብ ያለውን ብቻ ነው። ከወንዙ በስተ-ምስራቅ ያለውና እስከ ዘይላ ድረስ የተንጣለለው ምድር ወዲያውኑ ነበር ከእጁ ያፈተለከው። አባታቸው በዘይላ ሲገደል በስደተኝነት ወደ የመን የሸሹት አስራ አንዱ የሰዓደዲን ልጆች በ1415 ዓ.ል. ከስደት ተመልሰው በምስራቃዊው የኢፋት ግዛት ላይ አዲስ ሱልጣኔት መሰረቱ። ዋና ከተማቸውን ከሀረር አጠገብ በነበረችውና “ደከር” በምትባለው መሬት ላይ ቆረቆሩ። ዳግማዊ ሰብረዲን የሚባለውን የሰዓደዲን ልጅ በወላስማው ወንበር ላይ ካስቀመጡ በኋላ ህልውናቸውን በይፋ አበሰሩ። ከእንግዲህ ወዲያም ለማንም እንደማይገብሩና ሀገራቸውንም ከጥቃት እንደሚከላከሉ በይፋ አወጁ። ለአዲሱ ሱልጣኔትም “አዳል” የሚል ስያሜ ሰጡ።

የኢማም ኣህመድ ኢብን ኢብራሂም ኣል ጋዚ ዘመን

ታዋቂው ገዥ ኢማም አህመድ ኢብኑ ኢብራሂም አል ጋዚ በሱልጣኔቱ ላይ ትልቅ ተጽእኖ ነበረው። ከ በለው ጎሳ የተወለደው አህመድ ግራኝ እንደ ማህፉዝ ባሉ ሌሎች የሙስሊም ገዥዎች ስር ብዙ ቦታዎችን ካገለገለ በኋላ በ1527 ወደ ስልጣን መጣ። ግራኝ በተለምዶ በኢትዮጵያ ታሪክ አብያተ ክርስቲያናትን በማፍረስ እና ለክርስቲያኖች የማይራራ ሰው ሆኖ ይገለጻል። ይህን ለመደገፍ አንዳንድ ማስረጃዎች ሊኖሩ ቢችሉም፣ አህመድ ግራኝ እስካሁን ድረስ በሀገሪቱ ላይ ተጽእኖ ያላቸውን በርካታ ስኬቶችን ኣስመዝግብዋል። እንደ መሪ፣ በክርስቲያን ግዛት ላይ ብዙ ዘመቻዎችን መርቷል፣ እና ብዙ ጦርነቶች ላይ ልብነ ድንግልን እና ሌሎች ገዥዎችን አሸንፏል። በእርሳቸው አገዛዝ ወቅት ንግድ ለክልሎች ኢኮኖሚ ህልውና ቁልፍ ነገር ነበር እናም አዳል ከተለያዩ ሀገራት በተለይም ከኦቶማን ቱርክ ጋር ጠንካራ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት ነበረው። የእስልምና ሀይማኖት እንዲስፋፋም የጊዜው ነጋዴዎች ትልቅ ሚና ተጫውተዋል። ይህም እስከ ዛሬ ድረስ በኣካባቢው ለሚኖሩ ሙስሊሞች መብዛት ምክንያት እንደሆነ ይታመናል።

የአዳል ሱልጣኔት የተወለደው ከላይ በተገለጸው ሁኔታ ነው። በኢትዮጵያ ታሪክ ከታዩት ሱልጣኔታዊ መንግስታት ውስጥ እጅግ-ገናና ስም የነበረው ይኸው የአዳል ሱልጣኔት ነው። ይህ ሱልጣኔታዊ መንግስት የኢትዮጵያን ታሪክ ለመቀየር የቻሉትን እንደ አሚር ማሕፉዝ ሙሐመድ፣ ኢማም አሕመድ ኢብራሂም አል-ጛዚ (አሕመድ ግራኝ) እና አሚር ኑር ሙጃሂድን የመሳሰሉ ታላላቅ መሪዎችን አፍርቷል። በርካታ ጸሀፍት ስለርሱ ከትበዋል። በልዩ ልዩ ህዝቦች ስነ-ቃል ውስጥ እስካሁን ድረስ ያልቀዘቀዙ ወጎች እንዲከሰቱ ምክንያት ሆኗል። አሁንም ስለርሱ ታሪክ የሚያወሱ በርካታ ድርሳናት እየተጻፉ ነው። ከዚህ እልፍ ሲል ደግሞ “አዳል” የሚለው የሱልጣኔቱ መጠሪያ የሰው ስም ሆኖ ይገኛል። በተለይ የሚያስደንቀው ደግሞ በዚህ ስያሜ የሚጠሩት ከሙስሊሞች ይልቅ ክርስቲያኖች መሆናቸው ነው። ለዚህም ብዙዎች የሚያስታውሷቸውን እንደ ጋሻው አዳል፣ ዘሪኹን አዳልና ራስ አዳል ተሰማ (በኋላ ንጉስ ተክለ ሀይማኖት ተብለው በጎጃም የተሾሙት) የመሳሰሉ ስሞችን መጥቀስ ይቻላል። በሌላ በኩል የሰለሞናዊው አጼ መንግስት ከአዳል ሱልጣኔት ጋር በጦር ሜዳ እየተላለቀ ከነበሩት ክፍለ ጦሮች መካከል አንዱን “አዳል መብረቅ” በሚል ስያሜ ይጠራው ነበር። እርሱም በበኩሉ አዳልን እየጠላው ያደንቀው ነበር ማለት ነው። ከዚህ መረዳት እንደሚቻለው የሱልጣኔቱ ስመ-ገናናት በሁሉም ወገኖችና ህዝቦች ዘንድ ተደናቂነት ነበረው።

“አዳል” የሚለው ስም ምንጭ በትክክል አይታወቅም። አንዳንዶች “አዳ አሊ” (በአፋርኛ የአሊ ቤት ለማለት ነው) ከሚል ሥርወ-ቃል እንደተገኘ ይገምታሉ። አንዳንዶች ደግሞ ጥንት የሀረር አሚር ከነበረው “አሚር ኢዳል” ስም የተገኘ እንደሆነ ይናገራሉ። ሆኖም እርግጠኛው ነገር ላይ አልተደረሰም። የስያሜው ጥንታዊነት ግን በብዙ ምንጮች የተረጋገጠ ነው። ለምሳሌ አቡ ፈድሉላህ አል-ዑመሪ የሚባለው ግብጻዊ ምሁር በ1349 ዓ.ል. በጻፈውና “መሳሊከል አብሳር ፊ መማሊከል መሳር” በሚባለው ዝነኛ መጽሀፍ ውስጥ አዳል ተደጋግሞ የተጠቀሰ ስም ነው። ከ1415 ዓ.ል. በፊት “አዳል” በኢፋት ሱልጣኔት ስር የነበረ የአንድ አውራጃ ስም ነበር። የዐጼ ዐምደ ጽዮን (1314-1344 ዓ.ል) ዜና መዋዕል ዘጋቢ እንደጻፈው ከሆነ የዚህ አውራጃ ዋና ከተማ “ተላቅ” የሚል ስያሜ ነበረው። “ፉቱሕ አል- ሐበሽ” የተሰኘው መጽሀፍ ደራሲ ሱልጣኔቱን “አዳል” ከሚለው ስም በተጨማሪ “በሪ ሰዓደዲን” (የሰዓደዲን በር) እና “ዳር ሰዓደዲን” (የሰዓደዲን ሀገር) በሚሉ ስሞችም ይጠራዋል። ይህም ሱልጣኔቱን ያቋቋሙት የሱልጣን ሰዓደዲን ልጆች እንደ ሰማዕት በሚያዩት አባታቸው ስም ያወጡለት የክብር ስያሜ ነው። የግዕዝ ምንጮችም ስለኢትዮጵያ ኢስላማዊ ግዛቶች በሚጽፉበት ጊዜ “አዳል” የሚለውን ስም በእጅጉ ይደጋግሙታል። አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ስያሜው ከግዛት መጠሪያነት ያልፍና የኢትዮጵያ ሙስሊሞች በሙሉ በወል የሚጠሩበት ስም ሆኖ ይገኛል። በኢትዮጵያ ምድር ከታዩት ሱልጣኔቶች እምብዛም በማያደናግር ሁኔታ ታሪኩ የተጻፈለት “አዳል” ብቻ ነው (ከአንዳንድ አሻሚ ነጥቦች በስተቀር)። እጅግ ሰፊ ግዛት የሚያካልለውም “አዳል” ነው። ከሀረር ከተማ ታሪክ ጋር በእጅጉ የተቆራኘውም “አዳል” ነው።

አዳል በስፋቱም ሆነ በሕዝቦቹ ብዛት በኢትዮጵያ ምድር ከታዩት ሱልጣኔታዊ ግዛቶች በእጅጉ ይልቃል። በፕሮፌሰር ኡልሪች ብራውኬምፐር ጥናት እንደተገለጸው አዳል በስተምዕራብ በኩል ከባሊ፣ ደዋሮና ፈጠጋር(የአሁኗ ቢሾፍቱ) ጋር ይዋሰናል። በስተሰሜን በኩል ደግሞ እስከ አውሳ በረሃ መጨረሻ ድረስ ይደርሳል። በምስራቅ እስከ ኤደን ባህረ ሰላጤ የሚደርስ ሲሆን በደቡብ ደግሞ ከህንድ ውቅያኖስ ጋር ይዋሰናል። በአዳል ግዛት ውስጥ የኦሮሞ፣ የአፋር፣ የሶማሊ፣ የሀረላ (ሀረሪ) እና የአርጎባ ህዝቦች ይኖሩ የነበረ ሲሆን በዘመናችን በውል የማይታወቁ ሌሎች ህዝቦችም ነበሩበት። ዘይላ፡ አራ፣ በርበራ፣ ዳርዱራ፣ ሳሊራ፣ ሆበት፣ ጊዳያ፣ ሐርጋያ፣ ሀረር እና ኩሰም ከአዳል ከተሞች መካከል ጥቂቶቹ ናቸው። “ደከር” የሱልጣኔቱ የመጀመሪያ መዲና ነበረች፤ ከዚያም በዜይላ ተተካች፤ በስተመጨረሻም ሀረር የግዛተ መንግስቱ ዋና ከተማ ሆነች። አዳል የአዋሽ ወንዝ በሚፈስበት ክፍሉ እጅግ ለምና ለእርሻ ተስማሚ የሆነ መሬት ነበረው። አብዛኛው የሱልጣኔቱ ነዋሪ በግብርና ይተዳደር የነበረ ሲሆን ይህም የሰብል ማምረትንና የከብት እርባታን ያካተተ ነበር። በሌላ በኩል ሱልጣኔቱ የህንድ ውቅያኖስና የኤደን ባህረ ሰላጤ ተጎራባች መሆኑ ንግድ በክልሉ እንዲስፋፋ በእጅጉ ረድቷል። ዘይላ ሱልጣኔቱ ከውጪው ዓለም ጋር የሚገናኝበት ዋነኛ ወደብ ነበረች። የታጁራ፡ በርበራና መርካ ወደቦችም የሱልጣኔቱ አካላት ነበሩ። ከደቡብ፣ ከምዕራብና ከደቡብ ምስራቅ ኢትዮጵያ አካባቢዎች የሚመጡት የግብርና ውጤቶች፣ የዝሆን ጥርስ፣ ዝባድ ዘወተ.. ወደ ውጪ የሚላኩት በነዚሁ ወደቦች በኩል ሲሆን ከውጪው ዓለም የሚገቡ ሸቀጦችም ወደ ልዩ ልዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች የሚገቡት በሱልጣኔቱ ምድር ነው። ሰፊው የአዳል ሱልጣኔት በስሩ ያሉትን ክልሎች ሁሉ አንድ ወጥ በሆነ መንገድ አይደለም ያስተዳደረው። በስሩ ካሉት አካባቢዎች አንዳንዶቹ የራስ ገዝ አይነት አስተዳደር ነበራቸው። እነዚህ አስተዳደሮች “አሚር” የሚል ማዕረግ በነበራቸው ገዥዎች ይተዳደሩ ነበር። በአሚር ከሚተዳደሩት የአዳል ክፍለ ሀገራት በጣም ጎልተው የሚታዩት ዘይላ፣ ሁበትና ሀረር ናቸው።

“አዳል” ሱልጣኔቱ በታሪክ የሚታወቅበት ትክክለኛ ስም ነው። ይህም ከላይ እንደገለጽኩት በበርካታ የጥንት ሰነዶች ውስጥ የተመዘገበ ስያሜ ከመሆኑም በላይ የሱልጣኔቱ ገዥዎችና የሀገሬውም ህዝብ በመጠሪያነት ይጠቀሙበት ነበር። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን አንዳንድ ጸሀፍት ስያሜውን ከታሪክ ሰነዶች የማውጣት አዝማሚያ እየታየባቸው ነው። ምክንያቱን ባይነግሩንም ከሁኔታዎች መገመት የሚቻል ይመስለኛል። ይኸውም የ“አፋር ህዝብ ስያሜውን እንደ ስድብ ያየዋል” በሚል ሰበብ ነው። በርግጥም የአፋር ህዝብ “አፋር” ተብሎ ነው መጠራት ያለበት። ይህንንም በ1969 ዓ.ል. በገዋኔ ከተማ በተደረገው ታላቅ ጉባኤ ባሳለፈው ውሳኔ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝቦች አስታውቋል። እኛም ውሳኔውን በሙሉ ልባችን እናከብረዋለን። ስለዚህ “አዳል” የሚለው ስም የ“አፋር” ህዝብ መጠሪያ ሆኖ መቅረብ የለበትም። ነገር ግን በታሪክ ድርሳናት የሰፈረው “አዳል” የመንግስት ስም ከመሆኑ ውጪ የአፋር ህዝብን በተናጠል የሚመለከት ስያሜ አይደለም። ደግሞም ስያሜውን ለመንግስታቸው ያወጡት የጥንቱ ወላስማዎችና የሱልጣኔቱ ህዝቦች በዚህ ስም መጠራቱን ይወዱት ነበር። ዛሬ እኛ ተነስተን ጥንት “አዳል” ሲባል የነበረውን የሱልጣኔታዊ መንግስቱን ስያሜ “አፋር” ወደሚለው ከቀየርነው ታሪክ በጣም ይፋለሳል። ሱልጣኔቱ የበርካታ ህዝቦች ግዛት ሆኖ ሳለ የአንድ ህዝብ ብቻ አድርጎ ማቅረቡም ከባድ ስህተት ነው። ስለሆነም የጥንቱን ሱልጣኔት “አዳል” በሚለው ትክክለኛ ስሙ መጥራት ይገባል።

ከዚህ ጋር መጠቀስ ያለበት ሌላ ጉዳይ ደግሞ በ“አዳል” ታሪክ ላይ የሚደረገው የታሪክ ሽሚያ ነው። በዘመናችን የተለቀቁ በርካታ የኢንተርኔት ገጾች “አዳል” የሶማሊዎች ሱልጣኔት እንደነበረና ግዛቱም ሶማሊዎች የሰፈሩበትን አካባቢ (ሶማሊያ፣ ሶማሊላንድ፣ ኦጋዴን ወዘተ...) ብቻ እንደሚያጠቃልል አድርገው ነው የሚጽፉት። እነኝህ የኢንተርኔት ጽሁፎች አንድ የማያስተባብሉት ነገር ቢኖር “ሀረር የአዳል ዋና ከተማ ነበረች” የሚለው ብቻ ነው (ይህንንም ማስተባበል ያልቻሉት በፉቱሑል ሐበሽ ውስጥ የተጻፈ ሀቅ ስለሆነ ነው)። የሶማሊያው ጄኔራል ሙሐመድ ዚያድ በሬ በ1970 ኢትዮጵያን በወረረበት ጊዜም ይህንን የአዳል ሱልጣኔት ታሪክ እንደ ባለቤትነት ማረጋገጫ (justification) በማቅረብ “ከአዋሽና ዋቤ ሸበሌ ወንዞች በስተምስራቅና ደቡብ ያለው ግዛት በሙሉ የሶማሊያ ህጋዊ መሬት ነው” የሚል ፕሮፓጋንዳ ነዝቶ ነበር። ይሁንና ይህ ሁሉ ዐይን ያወጣ የታሪክ ዘረፋ ነው። በአዳል ግዛት ውስጥ ሶማሊዎች መኖራቸው እርግጠኛ ነገር ቢሆንም አዳልና የዛሬዋ ሶማሊያ በአፈጣጠራቸው፣ በማህበረ ህዝብ ተዋጾኦዋቸውና በታሪካዊ ጉዞአቸው በጭራሽ አይመሳሰሉም። አዳል የጥንታዊው የኢፋት ሱልጣኔት ቀጥተኛ ወራሽ (historical extension) ሆኖ ነው የተቋቋመው። የሱልጣኔቱ መሪዎችም በኢፋት (የዛሬው ሰሜን ምስራቅ ሸዋ ) አካባቢ ማዕከላቸውን ከቆረቆሩት የጥንቱ የወላስማ ሱልጣኖች የዘር ሀረግ ነው የተገኙት። የሱልጣኔቱ ዋና መስራች የሚባሉት ህዝቦች የሚኖሩትም በአሁኑ የኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ ነው። በአንድ ዘመን “አዳል” ሲባል የነበረው ስፍራ የተጠቃለለው በአሁኑ የኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ ነው (“አዳል እና ኢሳ” እና “ጨርጨር፣ አዳልና ጋራ ጉራቻ” የሚባሉትን አውራጃዎች ታስታውሱ የለም?)። የዛሬዋ ሶማሊያ አብዛኛው ክፍል በአዳል ሱልጣኔት ስር የነበረ ግዛት ቢሆንም ሱልጣኔቱ ታሪክ ሲሰራ የነበረውም ሆነ ታሪኩ የተቀበረው አሁን በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ ባለው ዋነኛ መሬቱ ላይ ነው። በአጭር አነጋገር የ“አዳል” መነሻም ሆነ እምብርቱ የነበረው በአሁኑ የኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ ነው። በሌላ በኩል አዳል በዘመኑ (ከ13ኛው እስከ 16ኛው ክፍለ ዘመን) የነበሩት የኢትዮጵያ ሱልጣኔታዊ ግዛቶች ሁሉ (ሀዲያ፣ባሌ፣ ደዋሮ፣ ሻርካ፣ ደራ፣ አራባባኒ ወዘተ..) የፖለቲካዊና መንፈሳዊ መሪ እንደነበረም የታሪክ ድርሳናት ያረጋግጣሉ። ዛሬ ከመላው የኢትዮጵያ ህዝብ 45 በመቶ ያህል የሚሸፍኑት ሙስሊም አማኞች መነሻም በነዚያ የጥንት ሱልጣኔታዊ ግዛቶች የሚኖሩት ሙስሊሞች ናቸው። በዚህ አንጻር ሲታይም የሱልጣኔቱ ታሪክ ህጋዊ ባለቤቶች መላው የኢትዮጵያ ሙስሊሞች እንጂ በ1960 ዓ.ል የተወለደው የሶማሊያ መንግስትና የ“ታላቋ ሶማሊያ” መፈክር አቀንቃኞች አይደሉም።

^ Herausgegeben von Uhlig, Siegbert, Encyclopaedia Aethiopica. Wiesbaden:Harrassowitz Verlag, 2003, pp.71

^ I.M Lewis, "The Somali Conquest of Horn of Africa," The Journal of African History, Vol. 1, No. 2. Cambridge University Press, 1960, p. 223.

(ምንጭ፡- አፈንዲ ሙተቂ፣ “ሀረር ጌይ-2”- የሀረርና የአዳል ታሪካዊ ወጎች፡ ገጽ 33-35) አዳል የምለው ስም የጉሣ ስም ይምሰልናል አፋር ውስጥ አዳአል ይምባል ጐሣ አለ ና አዳል የሚለው ስም የጐሣ ስም የምሰልናል

Axumitisk obelisk, Nordisk familjebok.png (ይህ ታሪክ ነክ ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። እርስዎ ሊያስፋፉት ይችላሉ!)

Last edited 3 months ago by 196.188.161.34

  1. ^ He was killed either in 805 AH / 1402-3 CE during the reign of Dawit I (according to al-Maqrizi) or in 817 AH / 1414-5 during the reign of Yeshaq I (according to a History of the Walashmaʿ edited by Cerulli 1931, p. 45); see Trimingham, J. Spencer (2013). Islam in Ethiopia. London: Routledge. p. 74, note 4. ISBN 9781136970221. https://books.google.com/books?id=UfrcAAAAQBAJ&pg=PA74.  Some historians pick one of the two possible dates (e.g. Paul Henze selects 1403 in Layers of Time, A History of Ethiopia [New York: Palgrave, 2000], p. 67).