የኮምፒዩተር(መንሰላስል) ምህንድስና የኤሌክትሪክና እና የኤሌክትሮኒክስ ምህንድስናን ከኮምፒዩተር ሳይንስ ጋር አዋህዶ የሚያጠና የእውቀት ዘርፍ ነው ። የኮምፒውተር መሃንዲሶች ብዙ ጊዜ የኤሌክትሮኒክስ ምህንድስናን፣ የሶፍትዌር እቅድና የተጨባጭ እና የማይጨበጥ የኮምፒውተር ክፍል ውህደት በማጠቃለል ያጠናሉ። እነዚህ መሃንዲሶች በብዙ አይነት የማንሰላሰል (ኮምፒውቲንግ) ስራ ላይ ይሳተፋሉ። ለምሳሌ በማይክሮፕሮሰሰር፣ በግል መንሰላስል (ኮምፒውተር) እና በታላላቆቹ መንሰላስሎች (ሱፐር ኮምፒውተሮች) ትልም ላይ ዋና ተዋንያን ናቸው። አልፎም ተርፎም በነዚህ ኮምፒወተሮች የሽቦወች ዑደት (ሰርኪዩት ዲዛይን) አቅድ አወጣጥ ሳይቀር ይሳተፋሉ። በዚህ ምክንያት የዚህ እውቀት ዘርፍ ተሳታፊወች አጠቃላይ የመንሰላስል ስርአት አካሄድን ብቻ ሳይሆን እንዴት መንሰላስሎች እርስ በርሳቸው እንደሚዋሃዱ ሁሉ ጥናት ያካሂዳሉ።

የመንሰላስል መሃንዲስ አብዛኛው ስራው የሚመለከተው 1) ሶፍትዌርና ፊርምዌር ለታቃፊ ማይክሮኮንትሮለሮች መጻፍ 2) VLSI የተሰኙትን የኮምፒውተር አካል ቁራጮች እቅድ መንደፍ 3) አናሎግ የስሜት ህዋሳትን መተለም 4) በቀጥተኛ እና በተርገብጋቢ ኤሌክትሪክ የሚሰሩ የተደባለቁ የሽቦ ዑደቶችን መዘየድ 5) ከዚያም ተርፎ የኮምፒውተር ኦፕሬቲንግ ስርዓትን መጻፍና መተለምን ያጠቃልላሉ።

የመንሰላስል መሃንዲሶች ከላይ በጠቀስናቸው ጥናቶች ስለሚሳተፉ የሮቦት ምህንድስናና ተመሳሳይ ቴክኖሎጂወች ላይ ከፍተኛ ተሳትፎ ማሳየት ይችላሉ።


የመንሰላስል ምህንድስና እንደ የዕውቀት ዘርፍ

ለማስተካከል

በአሜሪካን አገር የመጀመሪያው ህጋዊ እውቅና ያገኘ የኮምፒውተር ምህንድስና ዲግሪ ትምህርት የተሰጠው በ Case Western Reserve University በ1971 እ.ኤ.አ. ነው። ከጥቅምት 2004 እ.ኤ.አ ጀምሮ በአሜሪካ ውስጥ 170 የኮምፒውተር ምህንድስና ትምህርት የሚሰጡ ህጋዊ እውቅና የተሰጣቸው የትምህርት ቤቶች አሉ። ይህ የሆነበት ምክንያት ከምንጊዜም የበለጠ ከኮምፒውተር መሃንዲሶች የሚጠበቀው የስራ ተዋጾ እያደገ በመሄዱ ድሮ በሶፍትዌር መሃንዲሶች ወይም በኤሌክትሮኒክስ መሃንዲሶች የሚከናወኑት ስራወች መጠናቸው እየሰፋና በተወሰኑ የእውቀት ዘርፍ ባተኮሩ ጠበብት ብቻ የሚከናወኑ እየሆኑ በመሄዳቸው ነው። ኮምፒውተር ምህንድስና እንደ ኤሌክትሮኒክስ ምህንድስና የቀጥተኛና ተርገብጋቢ ኤሌክትሪክ ሽቦ ዑደት ትልም ያጠናል። እንደ ሌሎቹ የምህንድስና ትምህርቶች ከተማሪው ጠለቅ ያለ የሳይንስና የሒሳብ እውቀትን ይጠይቃል።

የኮምፒውተር ትልምና ጥቅም በጣም ሰፊ እየሆነ በመሄዱ አብዛኞቹ የክፍተኛ ትምህርት ተቆአማት ባሁኑ ጊዜ በጁኒየርና በሲኒየር የዩኒቨርሲቲ ቆይታቸው ባንድ በተወሰነ ርእስ ዙሪያ እንዲያተኩሩ ይመክራሉ። የIEEE/ACM Curriclum Guidlines እንደሚያመለክተው ዋና የኮምፒውተር ምህንድስና ክፍሎች በነዚ ይክፈላሉ [1] .

በኮምፒውተር ምህንድስና የሚጠናው የትምህርት ክፍል ከላይ በተጠቀሱት ብቻ አይወሰነም፤ እንዴያውም ከብዙ የምህንድስና ክፍሎች ሁሉ ጋር ተያያዥ ክፍሎች አሉት።

በአሜሪካን አገር አንድ ኮምፒውተር እንጂነሪንግ ተምሮ የተመረቀ ተማሪ በአማካይ $61738 ያገኛል። [2]

algorithm == ለተጨማሪ ማብራሪያ ==

ማጣቀሻወች

ለማስተካከል

የውጭ ተሳቢወች

ለማስተካከል
  1. ^ (እንግሊዝኛ) IEEE Computer Society (12 December 2004) Computer Engineering 2004: Curriculum Guidelines for Undergraduate Degree Programs in Computer Engineering. p. 12. http://www.computer.org/portal/cms_docs_ieeecs/ieeecs/education/cc2001/CCCE-FinalReport-2004Dec12-Final.pdf. Retrieved 2006-04-21.
  2. ^ (እንግሊዝኛ) CNNMoney.com (24 July 2009). Most Lucrative College Degrees Retrieved 2010-5-5.
  • 1. ^ IEEE Computer Society; ACM (12 December 2004). Computer Engineering 2004: Curriculum Guidelines for Undergraduate Degree Programs in Computer Engineering. p. iii. http://www.computer.org/portal/cms_docs_ieeecs/ieeecs/education/cc2001/CCCE-FinalReport-2004Dec12-Final.pdf. Retrieved 2006-04-21. "Computer engineering has traditionally been viewed as a combination of both computer science (CS) and electronic engineering (EE)."
  • 2. ^ Trinity College Dublin. "What is Computer Engineering". http://www.tcd.ie/Engineering/about/what_is_eng/computer_eng_intro.html. Retrieved 2006-04-21. , "Computer engineers need not only to understand how computer systems themselves work, but also how they integrate into the larger picture. Consider the car. A modern car contains many separate computer systems for controlling such things as the engine timing, the brakes and the air bags. To be able to design and implement such a car, the computer engineer needs a broad theoretical understanding of all these various subsystems & how they interact."
  • 3. ^ IEEE Computer Society; ACM (12 December 2004). Computer Engineering 2004: Curriculum Guidelines for Undergraduate Degree Programs in Computer Engineering. p. 5. http://www.computer.org/portal/cms_docs_ieeecs/ieeecs/education/cc2001/CCCE-FinalReport-2004Dec12-Final.pdf. Retrieved 2006-04-21. "In the United States, the first computer engineering program accredited by ABET (formerly the Accreditation Board for Engineering and Technology) was at Case Western Reserve University in 1972. As of October 2004, ABET has accredited over 170 computer engineering or similarly named programs."
  • 4. ^ IEEE Computer Society; ACM (12 December 2004). Computer Engineering 2004: Curriculum Guidelines for Undergraduate Degree Programs in Computer Engineering. p. 12. http://www.computer.org/portal/cms_docs_ieeecs/ieeecs/education/cc2001/CCCE-FinalReport-2004Dec12-Final.pdf. Retrieved 2006-04-21.
  • 5. ^ CNNMoney.com (24 July 2009). Most Lucrative College Degrees Retrieved 2010-5-5.