ካርኑቴስ በጥንት በጋሊያ (አሁን ፈረንሳይ) የተገኘ የኬልቶች ትልቅ ነገድ ነበሩ። ዋና ከተሞቻቸው የአሁኑ ሻርትረ እና ኦርሌያን ነበሩ። ግዛታቸው ለኬልቶች ፖለቲካዊና ሃይማኖታዊ ማዕከል ሲሆን የድሩዊዶች ጉባኤ በየዓመቱ በዚህ ይሰበሰብ ነበር። የራሳቸውን መሐለቅ ገንዘብ ይሠሩ ነበር። በ600 ዓክልበ. ካርኑቴስ ጣልያንን ከወረሩ ጎሣዎች መካከል እንደ ነበሩ ጸሐፊው ሊቪ ይለናል። ከ50 ዓክልበ. ከዩሊዩስ ቄሣር ዘመቻ ጀምሮ ለሮሜ መንግሥት ተገዥ ነበሩ።

የጋሊያ ወገኖች 100 ዓክልበ. ግድም