ኩታበር (ወረዳ) በአማራ ክልል በ ደቡብ ወሎ ዞን መሰተዳዳር ከሚገኙ 24 ወረዳዎች አንዱ ነው በወረዳው ውስጥ 20 የገጠር እና 1 ከተማ ቀበሌ በጠቅላላ 21 ቀበሌዎች አሉ

ኩታበር (ወረዳ)
ኩታበር (ወረዳ)
ኩታበር (ወረዳ) is located in ኢትዮጵያ
{{{alt}}}
ኩታበር (ወረዳ)

12°00′ ሰሜን ኬክሮስ እና 38°00′ ምሥራቅ ኬንትሮስ

ወረዳው ከደቡብ ወሎ ዞን ዋና ከተማ ደሴ በ20 ኪሜ ከክልል ዋና ከተማ ባህር ዳር በ500 ኪ.ሜ እንዲሁም ከኢትዮጵያ ዋና ከተማ አዲስ አበባ በ420 ኪ.ሜ እርቀት ላይ ትገኛለች፡፡

ወረዳው፡- 

በምሰራቅ ከ ተሁለደሬ

በምዕራብ ከ ተንታ

ከሰሜን አምባሰል

ከደቡብ ከ ደሴ ዙሪያ ትዋሰናለች ፡፡

የወረዳው ቆዳ ስፋት 70071 ሔ/ር ሲሆን አየር ንብረቱም 

ቆላማ 4% 

ደጋ 42 % 

ወይና ደጋ 54% ነው::

የወረዳው ዋና ከተማ የተቆረቆረቸው 1938 ጀምሮ በወቅቱ የአካባቢዊ ገዥ በነበሩት በአቶ ብርሃነ ስላሴና በደጅ አዝማች በላይ አሊ አማካኝነት እንደተቆረቆረ የከተማዋ የእድሜ ባለጸጋዎች ይናገራሉ የኩታበር ከተማ የዱሮ ስያሜዋ መታሎ በር ሲሆን ይህ ስያሜ የተሰጣት በአካባቢው መታሎ ተብሎ የሚጠራ ወንዝ በመኖሩ ከወንዙ ስም የተወሰደ ነበረ የአሁኑ ስያሜዋን ያገኘችበት ምክንያት የአገር ሽማሌዎች ሲናገሩ የደጃ አዝማች በላይ አሊ ዘመድ የሆኑት ሴት እሳቸውን ለመጠየቅ ወደ መታሎ በር መጥተው እንደነበረና አካባቢዊ ንፋሳማ በመሆኑ የለበሱትን ኩታ የንፋሱ ኃይል እያውለበለበ ሊውስደባቸው ሲሆን ኩታየን ያገርህ ንፋስ ሊቀማኝ ነው ብለው በመቀለዳቸው በዚህ አጋጣሚ ከሴትዮዋ ኩታ ጋር በማያያዝ ኩታበር እንደተባለች ያስረዳሉ ፡፡

ህዝብ ቆጠራ

ለማስተካከል

የኢትዮጵያ ማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ (CSA) በ 2007 ባካሄደው ብሔራዊ ቆጠራ መሠረት የዚህ ወረዳ ጠቅላላ የሕዝብ ብዛት 95.410 ነው።ይህም ቁጥር በ 1994 ከተደረገው የሕዝብ ቆጠራ የ 24.76% ቅናሽ ኣሳይቷል።ከዚህ ቁጥር ውስጥ 47,341 የሚሆኑት ወንዶች ሲሆኑ 48,069 ደግሞ ሴቶች ናቸው።4.940 ወይም 5.18% የሚሆኑት የከተማ ነዋሪዎች ናቸው።ከወረዳዋ ነዋሪዎች መካከል አብዛኞቹ ሙስሊም ናቸው። 87.83% የሚሆኑት የ ወረዳዋ ነዋሪዎች የ እስልምናን ሃይማኖት እንደሚከተሉ ሪፖርቱ ያስረዳል።እንዲሁም 12.01% የሚሆኑት ነዋሪዎች የ ኢትዮጵያ ኦርቶደክስ ተዋሕዶ እምነት ይከተላሉ።በሪፖርቱ ውስጥ በወረዳው 99.86% የሚሆነው ነዋሪ አማራ ነው።እንዲሁም አማርኛ 99.9% በመጀመሪያ ቋንቋነት ይነገራል።

ኩታበር (ወረዳ) አቀማመጥ

 
ኩታበር (ወረዳ)