ኦዶዋከር (425-486 ዓም የኖረ) በምዕራባዊው ሮሜ መንግሥት መጨረሻ ዘመን (468 ዓም) አንድ ጀርመናዊ አለቃ ሆኖ ጀርመናውያን ቅጥረኞች ሥራዊቱ በዓመጽ ተነስተው «የጣልያን ንጉሥ» የሚለውን ማዕረግ የወሰደው ነው። መጨረሻውን የምዕራባዊ ግዛት ንጉሥ (ቄሳር) ሮሙሉስ አውግስጦስ ዙፋኑን እንዲተው ካደረገ በኋላ የድሮ ሮማናውያን ሥልጣን በምሥራቅ (ቢዛንታይን) መንግሥትና ለጥቂት ዓመታት በሷሶን ግዛት ብቻ ቀረ። ኦዶዋካር በይፋ የምሥራቁ ቄሳር የዜኖ እንደራሴ ቢባልም፣ በተግባር ሮማ ከተማ እራሷ እንዲሁም መላው ጣልያን ከዚህ ጀምሮ በጀርመናውያን ቅጥረኞቹ (ሄሩላውያንስኪራውያን ነገዶቹ) ትገዛ ጀመር።

የኦዶዋከር ምስል በ469 ዓም መሐለቅ

የታሪክ ጸሐፊ ዮርዳኔስ እንደሚለን ከዚያ በፊት በሕዝቡ ዘንድ የኦዶዋከር ማዕረግ «የቱርኪሊንጊ ንጉሥ» ተብሎ ነበር፤ እነዚህም «ቱርኪሊንጊ» ባብዛኛው ሊቃውንት አስተያየት በጀርመናዊ ቅጥረኞቺ ነገዶች መካከል አንድ ጥቃቅን ጎሣ ሲሆኑ፣ ዳሩ ግን ከዚህ መረጃ ኦዶዋከር ከቱርኪክ ዘር እንደ ነበር የሚያስቡ መምህሮች ደግሞ ተገኝተዋል። የድሮ ጸሐፊዎች በተጨማሪ እንደሚመሰክሩልን፣ የኦዶዋከር አባት ኤዴኮ ሲሆን ለሁኖች አለቃ ለአቲላ ልዩ ተልእኮ ሆኖ ነበር፤ ይህ ግን ጀርመናዊ አለመሆኑን ምንም አያስረዳም።

በመጀመርያው ኦዶዋካር ለዜኖ በቁስጥንጥንያ ወዳጅ መልክ ቢያሳይም፣ ከ476 ዓም በኋላ ግን የዜኖ አለቃ ኢሉስ ባመጸበት ጊዜ፣ ኦዶዋከር ለኢሉስ እርዳታውን ስለ ሰጠ፣ ዜኖ በፈንታው ሌሎች ተወዳዳሪ ጀርመናውያን ብሔሮች፣ ሩጋውያን ከዚያም ኦስትሮጎታውያን ጣልያንን እንዲወርሩ ላካቸው። ከብዙ ትግል በኋላ በ486 ዓም የኦስትሮጎታውያን ንጉሥ ጤዮደሪክ ጣልያንን ይዞ ኦዶዋከርን በገዛው እጁ ገደለው።