እንደወጣች ቀረች
«እንደወጣች ቀረች» 189 ገጾች ያሉትና በ፲፱፻፵፮ ዓ.ም. የተፃፈ ሲሆን በውስጡም ከ፲፱፻፳፰ እስከ ፲፱፻፴፫ ዓ.ም. በኢትዮጵያ ላይ የተፈፀመው የኢጣልያ ወረራና በኢትዮጵያ ታሪክ ላይ ያመጣው አያሌ ቀውሶች በሰፊው ያትታል። በተለይም በህዝቡ መንፈስ ላይ፣ በአገሪቱ ልማድና የኑሮ ባህል ላይ በአጠቃላይ በማህበራዊ ህይወቱ ላይ ታላቅ ቀውስን ያስከተለ መሆኑንም ያብራራል።
የነበረውን የጦርነት አስከፊነት መጽሐፉ ሲያትት ኢጣሊያኖች እጅግ ጨካኞች ነበሩ። በተለይም ከሀገሬው ተወላጆች በልዮ ልዩ ምክንያት በዘመኑ በእስር ላይ የነበሩትን በመፍታት ለራሳቸው ባንዳ አድርገው ከመለመሏቸው በኋላ ከአርበኞች ጋር ያዋጓቸው ነበር። ሀገሬውን እርስ በርሱ በማዋጋት ህዝቡን ጨርሶ ሀገሪቷን ለመውረስ ከፍተኛ እቅድ ነበራቸው። አርበኞች ግን የምግብ ችግር፣ የክረምቱ መጫንና የበረሀው ኑሮ ሳያግዳቸው ቤት ሀገር ነው ሀገር ከሌለ ቤት የለም በማለት ለባዕድ መገዛት አሻፈረኝ ብለው ለነፃነታቸው በየዱሩ እንደተዋጉም ያወሳል።
ፀሀፊው በመጽሐፉ በሰፊው ሊያሳይ የሞከረው ሀሳብ በኢጣልያ ወረራ ምክንያት በሀገሪቱ የተስፋፋው የሴተኛ አዳሪነት አስከፊ ህይወት ነው።
ይህ ዘመን የሰው ስብዕና የተዋረደበት፣ ገንዘብ ከሰው ይልቅ የተወደደበት፣ ፍቅርና ዘመድ ወደ ገንዘብ የተለወጠበት ዘመን ነበር። ከዚህም የተነሳ በከተማ ሲኖር ባለትዳር ከመሆን ይልቅ ሴተኛ አዳሪ መሆን ሰፊ ነፃነትና ደስታም ያለበት ኑሮ ነው ተብሎ የታመነበት ዘመንም ነበር።
ሌላው የማህበራዊ ኑሮ ቀውስ ነው ብለው ጸሐፊው በስፋት ያተቱት ስለመጠጥ ጠንቅ ነው። በኣጠቃላይ ደራሲው ይህንን ሁሉ የማህበራዊ ህይወት ቀውሶች ያመጣው የኢጣሊያ መምጣት ነው። ላይጠቀምበት የሰው ሀገር ወሮ፣ የሰውንም ቤተሰብ በትኖ፣ የሰውንም ትዳር አጥፍቶ ፣ የሰውንም ምግባር አበላሽቶ ከፈላስፋዎች መካከል ዓለም እንደ ፈጣሪው የመጀመሪያው ነው። መጀመሪያና መጨረሻ የለውም ፍጡር ከፈጣሪው አይለይምና ይህም አባባል የፈላስፋው የአርስጣጣሊስ ሲሆን ከእርሱ በኋላ በኋላ የፊሊጶስ ልጅ የእስክንድር፣ ሴቶቹንም ቅጥ በሌለው ኑሮ ዕድሜያቸውን እንዲጨርሱ አደረጋቸው በማለት ሴተኛ አዳሪነትን በእጅጉ የሚቃወም ሲሆን በተጨማሪም ከዚህ በፊት ይህ ምግባር ከነውር ይቆጠር ነበር ነውርነቱ የተሻረው በኢጣሊያኖች ጊዜ እንደሆነ ስለተረዳሁ ለወገኖቼ ይህንን የመሰለ ኑሮ የማያዘልቅ ስለሆነ አዲሶቹም እንዳይታለሉ የገቡትም ወደ ወትሮው ትዳራቸው እንዲመለሱ የሚሻል ነው በማለት ይህንን ልብወለድ መፅሐፋቸውን መታሰቢያነቱ ለኢትዮጵያውያን ሴቶች እንዲሆን በማበርከት ፅፈዋል።
ማጣቀሻ
ለማስተካከል- ናሽናል ቢብሊዮግራፊ ቡድን፣ መዝገበ ህትመት ዳሰሳ፣ ቅፅ 25፣ ቁጥር 5፣ 2000 ዓ.ም.፣ ገፅ 14-15 Archived ጁላይ 20, 2011 at the Wayback Machine
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |