ኤ ናይት ቱ ሪመምበር (የሻላማር ዘፈን)


«ኤ ናይት ቱ ሪመምበር» (A Night To Remember) ከ1982 እ.ኤ.አ. (1974 ዓም) የሆነ የሻላማር ነጠላ ዘፈን ነው። ከስድስተኛ አልበማቸው ፍሬንድዝ ነው። በዚያው አመት በአሜሪካ እስከ #44 ሥፍራ፣ በእንግሊዝም እስከ #5 ድረስ ፈለቀ። ዘፈኑም በኋላ በቀረጹት ሌሎች ቡድኖች፣ ሂፕ-ሆፕ ቅመሾችና በፊልሞች፣ ማስታወቂያዎች ተጨማሪ ዕውቀና አግኝቷል።

«ኤ ናይት ቱ ሪመምበር»
ሻላማር 1983 እ.ኤ.አ.
ሻላማር ዘፈን ከፍሬንድዝ አልበም
የተለቀቀው ፌብሩዋሪ1982 እ.ኤ.አ.
የተቀዳው 1981 እ.ኤ.አ.
ስልት ፋንክድኅረ-ዲስኮ
ርዝመት 5:08
ቋንቋ እንግሊዝኛ
አሳታሚ ሊያን ስልቨርስ ፫ኛ
ግጥም ናይድራ ቢርድ፣ ደይና ማየርዝ፣ ሻርሜን ስልቨርዝ
ቅንብር ሶላር ሬኮርድስ