ኤድመንድ ሂለሪ
(ከኤድሙንድ ሂለሪ የተዛወረ)
ኤድመንድ ሂለሪ (እንግሊዝኛ፦ Edmund Hillary) ከ1911 እስከ 2000 ዓም የኖሩ የኒው ዚላንድ ተጓዥ ነበሩ። በተለይ ተራራ ጫፎች የወጣ ተጓዥ ነበሩ። መጀመርያ ወደ ዓለሙ አብልጦ ሸከፍተኛ ቦታ ወደ ኤቨረስት ተራራ ጫፍ የወጣው ሰው ልጅ ከመሆናቸው በላይ፣ እስከ ደቡብ ዋልታ እንዲሁም እስከ ስሜን ዋልታ ተጓዙ።የአለማችንን በረዶአማ ቦታዎች እና ትላልቅ ተራራዎችን በመዉጣት ይታወቃሉ::