ኤሌክትሪክ ምድጃ ፡ እራስህ ስራ

ኤሌክትሪክ ምድጃ፡ እራስህ ስራ እንዴት አንድ ሰው በቀላሉ በኤሌክትሪክ የሚሰራ ምድጃ በመስራት ከእንጨት ለቀማ እና ክሰል ማክስል ውጭ በኤሌክትሪክ ምግብ መስሪያ እንደሚሰራ የሚያሳይ ነው። ማናቸውም የእራስህ ስራ ተግባራት በሚያውቅ ሰው ቁጥጥር ስር የሚሰሩ እንጂ እንዲሁ ያለእውቀት እንዲሰሩ ክልክል ነው። በተለይ ማናቸውም የኤሌክትሪክ እቃወች በከፍተኛ ጥንቃቄ መሰራት ይገባቸዋል።

ቀላል ኤሌክትሪክ ምድጃ

በጣም ቀላል የኤሌክትሪክ ምድጃ ለመስራት የሚያስፈልጉ ነገሮች፡

1- ሁለት መካከለኛ የብረት ዝርግ ሳህኖች።

2- በኒህ ሳህኖች ልክ የተከረከመ ክብ የሸክላ ምጣድ።

3- ሁለት ማጣበቂያ ብሎኖች።

4- 1ፓውንድ የአለት ሪዝ

5- አንድ ረዘምና ሰፋ ያለ ጣውላ (ውፍረቱ 3 ሳንቲ ሜትር፣ ስፋቱ 36 ሳንቲ ሜትር ፣ ርዝመቱ 45 ሳንቲ ሜትር)

6- አንድ ማብሪያ ማጥፊያ

7- አንድ (4 አምፔይር) ፊውዝ

8- 80ጫማ የኤሌክትሪክ ጥቅልል ሽቦ

9- ሁለት ረዥም ብሎኖች

10- የክብ ወገባቸው ግማሽ ሳንቲ ሜትር የሚሆን ሁለት የብርጭቆ ቱቦወች

11- 3 ባለ 6 ሳንቲ ሜትር ብሎኖች

ስዕል 1 ላይ እንደሚታየው ታችኛ ሳህን ላይ 6 ቀዳዶች ይበሳሉ (ይነደላሉ)። ከአራቱ ቀዳዶች፣ ሁለቱ ሳህኑ ጥርዝ ላይ ይደረጋሉ። 6ቱም ቀድዶች በአንድ ቀጥታ መስመር ላይ ይበሳሉ። ከአራቱ አንዱ ሳህኑ መሃል ላይ ይበሳል፣ ሌሎቹ እርስ በርሳቸው በ6 ሳንቲ ሜትር ይራራቃሉ። ስዕል 2 ላይ እንደሚታየው ላይኛ ሳህን ሁለት ብቻ ቀዳዳ ሲነደል፣ ሁለቱም ቀዳዶች የሳህኑ ጠርዝ ላይ ይደረጋሉ፣ እኒህ ሁለት ቀዳዶች ከታችኛ ሳህን ሁለት የጠርዝ ቀዳዶች ትይዩ መሆን ይገባቸዋል። ከቆርቆሮ ወይም ሌላ ብረት የተሰራ አቃፊ የብረት ኮሌታ ስዕል 3 ላይ እንደሚታየው ያስፈልጋል። ይህ ከብቢ የብረት ኮሌታ ታችኛ ሳህንን በትክክል ማቀፍ እንዲችል ተደርጎ የተሰራ መሆን አለበት፡፡ ኮሌታው ከስሩ ሁለት ምላሶች ተቀደው ይወጡለትና እኒህ ምላሶች በብሎን ከጣውላው ጋር በብሎን ይታሰራል።

  • ከጣውላው ላይ ለሁለቱ የብርጭቆ ቱቦወች መግቢያና መውጫ የሚሆን ቀዳዶች ይበሳሉ። ከዚያ ሁለቱ ቱቦወች በጣውላው ቀዳዳ ውስጥ ይገባሉ። የቱቦወቹ ርዝመት እንግዲህ 13 ሳንቲ ሜትር ነው። እንግዲህ ቱቦወቹ በትክክል የተቆረጡ ከሆነ ከብረት ኮሌታው በላይ በ1 ሳንቲ ሜትር ይረዝማሉ።
  • ቀጥሎ ከብረት ኮሌታው አፍ 2 ሳንቲ ሜትር ዝቅ ብሎ ያለውን ክፍል በሙሉ በአለት ሪዝ ተጠቅጥቆ ይሞላል (የብረት ሪዙ ዋና ተግባር ሙቀት እንዳይተላለፍ ማድረግ ነው - የአለት ሪዝ ከሌለን ሙቀት የማያስተላልፍ ሌላ ነገር በአለት ሪዙ ቦታ ሊቀመጥ ይችላል)። ይህ እንግዲህ የታችኛ ሳህኑ ተመቻችቶ በአለት ሪዙ ላይ እንዲቀመጥ ይረዳል። የሳህኑ ጠርዝ ከብረት ኮሌታው አፍ ላይ በሚገባ መቀመጥ አለበት።
  • ስዕል 3 ላይ እንደሚታየው፣ የታችኛ ሳህኑ ከጣውላው ጋር በሁለት ረጃጅም ብሎኖች ይያያዛል።
  • ፊውዝና ማብሪያ ማጥፊያ ከጣውላው ጋር በብሎን ከታሰሩ በኋላ፣ በጣውላው ስር በሚበሱ ቀዳዶች የኤሌክትሪክ ገመዶቹ ስዕል 4 ላይ በሚታይ መልኩ በብርጭቆ ትቦወቹ በመሄድ ከምድጃው ጋር ይያያዛሉ።
  • ለምድጃው ዋና ክፍል ቢኖር ጥቅልል ሽቦው ነው። ጥቅልል ሽቦው ኤሌክትሪክ ሲያልፍበት በመጋል ሙቀት የሚሰጥ ክፍል ነው። ነገር ግን የተለያየ የጥቅልል ሽቦ ርዝመት የተለያየ ሙቀት ይሰጣል፣ በጣም ረጅም ገመድ አንስተኛ ሙቀት ሲሰጥ በጣም አጭር ደግሞ ከፍተኛ ሙቀት ይሰጣል። ስለሆነም መጀመሪያ ትቅልል ሽቦውን የሸክላ ጡቦች ፈልጎ በነዚህ ጡቦች ላይ መጠቅለል ያስልፈልጋል። እንግዲህ እነዚህ ጡቦች ወደ ጎን ይቀመጡና አንዱ ጎን ከፊውዝ ጋር ተገናኝቶ ሌላው ጎን ከሶኬት ጋር ተገናኝቶ ሶኬቱ ከግድግዳ ሶኬት ላይ ይሰካል። በዚህ ወቅት ጥቅልል ሽቦው ይፍማል። ሽቦው ብዙ ክልፋመ፣ ከፉውዙ የሚሄደውን ገመድ በማንሳት የጥቅልል ሽቦውን ርዝመት እየቀነሱ ሽቦው በሃይል ሳይግም፣ በጣምም ሳይቀዘቅዝ፣ በመካከል፣ ደብዘዝ ያለ ቀይ በሆነ ሁኔታ በሚሰጥበት ርዝመት መቁረጥ ነው። በምንም ሁኔታ፣ ማናቸውም ሽቦወች ከማንኛውም የሰውነት ክፍል ጋር በዚህ ወቅት መነካካት የለባቸውም። ትክክለኛው ርዝመት ሽቦ ከተቆረጠ በኋላ ሽቦው ከረጅም ዘንግ ላይ ይጠመጠማል። ይህም ምክንያቱ

ሽቦው ቀልጠፍ ብሎ በሸክላው ላይ በሚሰራ ዚግዛግ ላይ እንዲያርፍ ነው።

  • እንግዲህ ሸክላው ከታችኛ ሳህን በ1ሳንቲ ሜትር ከፍ ያለ ሆኖ ከታችኛ ሳህን ላይ ይገጠማል። በዚህ ሸክላ ላይ በተቀረፀ ዚግዛግ ውስጥ ለውስጥ ጥቅልል ሽቦው ይሽሎኮሎካል። ይህ ሽቦ በምንም መንገድ የላይኛ ሳህን እንዳይነካ እንዲሁም እርስ በርሱ እንዳይጋጭ ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል። ከዚህ በኋላ የሽቦወቹ ጫፎች በብርጭቆ ቱቦወቹ አድርገው ከሚመጡት የኤሌክትሪክ ሽቦወች ጋር ይያያዛሉ። የፊውዝ ገመድ ከፊውዙ ሳጥን ውስጥ ከገባ በኋላ ወደ ማገናኛ ብሎኑ ከተወሰደ በኃላ ከዚያ ወደ ሶኬት ገመዱ ይተላለፋል። ከዚያ በኃላ የላይኛ ሳህን ከስዕሉ ላይ በሚታዩ ብሎኖች ከሌላው ክፍል ጋር ይጋጠማል። በዚህ መንገድ ስራው ይጠናቀቃል። [1]

ማጣቀሻ ለማስተካከል

  1. ^ "The Boy Mechanic Vol. 1", by Popular Mechanics Co