የኢድ አላድሃ በዓል በሙስሊሞች ነብዩሏህ ኢብራሒም ልጃቸውን ነብዩሏህ ኢስማኢልን በአረፋ ተራራ ላይ በአላህ ትዕዛዝ ሊሠዎ የነበረበት ቀን የሚከበርበት በአል ነው። ነገር ግን ለአላህ ምስጋና ይገባውና በምትኩ በአላህ ትዕዛዝ በግ ሊያርዱ በቅተዋል። ይህን በአል የእስልምና እምነት ተከታዮች ወደ መስጂድ በመሄድ እና ሶላት በመስገድ ያከብራሉ።

: