ኢዩግሊና
ኢዩግሊና

ኢዩግሊና ባለ አንድ ሕዋስ ዘአካል ነው፡፡ ይህ ዘአካል በተፈጥሮ አይን አይታይም፡፡ በማይክሮስኮፕ እገዛ ግን ማየት ይቻላል፡፡ ኢዮግሊና የእንቁላል ቅርፅ ያለው ሲሆን ወደ ጭንቅላቱ ቀጭን ነው፡፡ የኢዮግሊና መዋቅር ሕዋስ ክርታስ፣ ተኮማታሪ ፊኝት፣ ልምጭት፣ የአይን ነጥብና አረንጓአቀፍ ናቸው፡፡

ኢዩግሊናን ከእፅዋትና ከእንስሳት ጋር የሚያመሳለው ባህሪይ

ለማስተካከል

ኢዮግሊና የእፅዋትና የእንስሳት ባህርይ አለው፡፡ እንደእንስሳት ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስ ይችላል፡፡ አረንጓአቀፍ ስላለው እንደ እፅዋት ደግሞ የብርሃን አስተፆምር ማካሄድ ይችላል፡፡

የኢዩግሊና ምቹጌ

ለማስተካከል

ኢዮግሊና በጉድጓድ ውኃና በኩሬ ውሃ ውስጥ ይኖራል፡፡

የኢዩግሊና እንቅስቃሴ

ለማስተካከል

ኢዩግሊና የመንቀሳቀሻ አካል አለው፡፡ ይህም አካል ልምጭት ይባላል፡፡ ልምጭት ተጠቅልሎ ሲወዛወዝ ኢዩግሊና እንቅስቃሴ ያደርጋል፡፡

የኢዩግሊና አመጋገብ

ለማስተካከል

ኢዩግሊና አረንጓዴ ሐመልማል ስላለው የፀሐይ ብርሃን ሲያገኝ ምግቡን ማዘጋጀት ይችላል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ለረጅም ጊዜ በጨለማ ውስጥ ከቆየ ምግብን ማዘጋጀት አይችልም፡፡ ስለዚህ በውኃ ውስጥ የሟሙ ምግቦችን ይመገባል፡፡

ኢዩግሊና እንዴት ይራባል?

ለማስተካከል

ኢዩግሊና በኢፆታዊ /ክልኤ ቁርስት/ በሁለት በመከፈል ይራባል፡፡ በመጀመሪያ ኑክለስ ለሁለት ይከፈላል፡፡ በመቀጠል ቤተ-ሕዋስም ይከፈላል፡፡ በመጨረሻም ሁለት አዳዲስ ሕዋሶች ይፈጠራሉ፡፡

የኢዮግሊና ጥቅም

ለማስተካከል

በሥነሕይወታዊ ጥናትና ምርምር ውስጥ ይጠቅማል፡፡ የብርሃን አስተፃምር ስለሚያካሄድ ኦክስጂንን ለማምረት ያገለግላል፡፡[1]

  1. ^ የስምንተኛ ክፍል ባዮሎጂ የተማሪ መጽሐፍ