ኢንጅነር ቅጣው እጅጉ ኢትዮጲያዊ አሜሪካዊ የጠፈር ተመራማሪ ሲሆን በአሜሪካ የብሔራዊ የጠፈር ምርምር አስተዳደር (NASA) ውስጥ በተመራማሪነት ሰርቷል።[1] ሲሆን ከሌሎች መሃንዲሶችና ሳይንትስቶች ጋር በመተባበር ለእኛ አለም (Planet Earth) እና ለተቀሩት ፕላኔቶች የምርምር ሳይንስ (Planetary Science Research and Exploration) የሚረዱ የጠፈር መንኮራኩሮችና ሮኬቶች ፈጥረዋል።

ውልደት እና አስተዳደግ

ለማስተካከል

ዶክተር ኢንጂነር ቅጣው እጅጉ የካቲት 25 ቀን 1948 (እ.ኤ.አ) ከአባታቸው ከአቶ እጅጉ ሃይሌ እና ከእናታቸው ከወ/ሮ አስካለ በላይነህ በከፋ ጠቅላይ ግዛት በቦንጋ ከተማ ተወለዱ።[2] የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በቦንጋ፣ በዋከና በጅማ ከተማ ካጠናቀቁ በኋላ በባህር ዳር በሚገኘው ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የከፍተኛ ትምህርታቸውን አጠናቀዋል። ዶክተር ቅጣው ወደ ጃፓን አገር በመሄድ በኦሳካ ዪኒቨርስቲ በቋንቋና የጃፓን ኢኮኖሚ፣በሄሮሺማ ዩንቨርስቲ የኢንደስትሪ እና የአውቶሞቲቭ ኢንጂነሪንግ አጥንተው ትምህርታቸውን አጠናቀዋል። በኋላም አሜሪካን ሀገር ስኮላር ሺፕ አግኝተው በቢዝነስ አድሚንስትሬሽን ማስትሬታቸውን በመጨረሻም ለትምህርት ባላቸው ከፍተኛ ፍላጎት በኤሮ-ስፔስ ምህንድስና ዶክትሬታቸውን ተቀብለዋል።

  1. ^ "Archive copy". Archived from the original on 2023-02-02. በ2023-09-16 የተወሰደ.
  2. ^ https://www.thefamouspeople.com/profiles/kitaw-ejigu-5703.php