ኢንዳክተር ብዙ ጊዜ ከኤሌክትሪክ አሳላፊ ቁስ ጥምጥም የሚሰራ የኤሌክትሪክ መሳሪያ ነው። ለምሳሌ በብረት ዘንግ ላይ የተጠመጠመ የመዳብ ሽቦ ኢንዳክተር ይፈጥራል። የተጠመጠመበት ነገር የበለጠ መግኔታዊ እየሆነ በሄደ ቁጥር በኢንዳክተሩ ዙሪያ የሚፈጠረው መግነጢሳዊ መስክ የበለጠው ወደ ዘንጉ ውስጥ ስለሚገባ እልከኝነቱ እያደገ ይሄዳል[1]

የተለያዩ የኢንዳክተሮች ዓይነቶች

ኢንደክተሮች እንዴት ነው ሚሰሩ?

ለማስተካከል

ካፓሲተሮችቮልቴጅ ለውጥን እንደሚጠሉ ሁሉ ኢንደክተሮች በተራቸው የኤሌክትሪክ ጅረትን ለውጥ ይጠላሉ። ባጠቃላይ መልኩ ፣ በጊዜ የሚለዋወጠው የኢንደክተሩ ቮልቴጅ v(t) እና እልክኝነቱ L እና በውስጡ የሚያልፈው ተለዋዋጭ የኤሌክትሪክ ጅረት i(t) ዝምድና በሚከተለው የለውጥ እኩልዮሽ ይገለጻል:

 

በምሳሌ ለመረዳት፣ አንድ በጣም ከባድ የውሃ ተሽከርካሪ ከወንዝ ዳርቻ ቢሰራ፣ ወንዙ በስሩ ሲያልፍ ከክበደቱ አንጻር ለመሽከርከር መጀመሪያ እምቢ ይላል። አንዴ መሽከርከር ከጀመረ በኋላ ደግሞ፣ የወንዙ ፍሰት ሲቋረጥ እርሱ ግን መሽከርከሩን ባለማቋረጥ ውሃው እንዲፈስ ያደርጋል፣ በስብቀት ምክንያት ሃይሉ ተሟጦ እስካቆመ ድረስ። ኢንደክተርም እንዲሁ ነው። መጀመሪያ የኤሌክትሪክ ጅረት ሲገጥመው አላሳልፍም በማለት እልክ ይገባል። ሆኖም ቀስ ብሎ እየተላመደ ይሄድና በኋላ የኤሌክትሪክ ጅረቱ ምንጭ ሲቋረጥ እርሱ እራሱ ጅረቱን በመግፋት የኤሌክትሪክ ጅረቱ እንዲቀጥል ያደርጋል።

የኢንደክተሮች ተግባራዊ አጠቃቀም

ለማስተካከል

ኢንደክተሮች ብዙ ጊዜ ጥቅም ላይ የሚውሉት በአናሎግ ዑደቶች ውስጥ ነው። የመግነጢስ ፍሰታቸው የተጣመሩባቸው ኢንደክተሮች በጣም ጠቃሚ የሆነውን ትራንስፎርመር የሚባለውን የኤሌክትሪክ መሳሪያ ይፈጥራሉ። ኢንዳክተሮች በኤሌክትሪክ ስርጭት መስመሮች ላይም እንዲሁ የሚፈጠሩ ቮልቴጆችን ለመቀነስና የተሳሳቱ ጅረቶችን ለማስተካከል ይረዳሉ።

  1. ^ "Inductors 101". Vishay Intertechnology, Inc. (2008-08-12). በ2010-10-02 የተወሰደ.

ተጨማሪ ንባብ

ለማስተካከል