ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ቅደሚ

"ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ቅደሚ"ደርግ ዘመነ መንግሥት የኢትዮጵያ ብሔራዊ መዝሙር ነበር።

ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ቅደሚ
በኅብረተሰባዊነት አብቢ ለምልሚ!
ቃል ኪዳን ገብተዋል ጀግኖች ልጆችሽ
ወንዞች ተራሮችሽ ድንግል መሬትሽ
ለኢትዮጵያ አንድነት ለነፃነትሽ
መስዋዕት ሲሆኑ ለክብር ለዝናሽ!
ተራመጂ ወደፊት በጥበብ ጎዳና
ታጠቂ ለሥራ ላገር ብልጽግና!
የጀግኖች እናት ነሽ በልጆችሽ ኩሪ
ጠላቶችሽ ይጥፉ ለዘላለም ኑሪ!


ግጥም: አሰፋ ገብረማርያም
ዜማ: ዳንኤል ዮሐንስ