ኢትቢራ ፦ይህ ቃል ሁለት ጥምር ቃላትን በአንድ ላይ የያዘ ስሆን ስነጣጠል <iitto=biiraa>ወይም ኢቶ=ቢራ የሚል ነው።

እና ይህ ትርጉሙ ምን ማለት እንደሆነ እና እንዴት እንደተቀየረ እንመልከት።

ቦተው የሚገኛው በደቡብ ቤሔር ቤሔረሰቦችና ህዝቦች ክልላዊ መንግስት በሀድያ ዞንጊቤ ወረዳ ውስጥ ሲሆን  የስሙም ትርጉም [Itto-ፍቅር; biira አደባባይ] ማለት ነው።

እውነትም የፍቅር አደባባይ ለመባል ያበቁ ምክኒያቶች አሉት። ስፍረው የፍቅር አደባባይ ከመባል በፊት የእሾህ አደባባይ ተብለው ነበር ሲጠራ የነበረው። ስሙ ኢትቢራ እንዲባል ያደረጉ ምክኒያት _ቤተክርስቲያን _ትምህርት ቤት _ገበያ

በኢትዮጵያውያን አቆጣጠር በ1987 ዓም ላይ በአቶ ኤርጡሞ ደምሴ ደጅ ቤተ ክርስቲያን ተመሰረተ። በአጠቃላይ ሶስቱ ንኡስ ማለትም የአሁኑ ኢትቢራ፣ ጎዶዶዋለሜ በአንድ ላይ ከሚያመልኩበት ለሁለት ተከፍሎ ከጎዶዶ ወደ ኢትቢራ እንዲመጣ ሶስት ምክኒያቶች ነበሩ።

1፦ የቦታው ርቀት __>> ከላይኛው ኢትቢራ ምእመኑ ለአንልኮ በእግር ተጉዘው ለመሄድ ትራብስፖርት የሚጠይቅ ርቀት አለው ያን ለማድረግ ደግሞ ትራንስፖርት አለመኖሩ!!

2፦የአዳራሹ ጥበት __>> ሶስቱ ንኡስ በኣንድ አዳራሽ ለመቀመጥ ቦታ በቂ አልነበረም አብዛኛው ሰው በውጭ ይቀመጥ ነበት። በወቅቱም ላይ ብዙ ጌታን የሚቀበሉ አዳዲስ ሰው ቁጥርም በጣም እየጨመረ ስለነበረ ።

3፦ቤተክርስትያኑ የተቋመው በግለሰብ መሬት መሆኑ ሌሎችም ግን በነዝህ በ3 ዋና ጉዳይ ላይ ባተኮሩ የግለሰብ ግፊት ነው ከጎዶዶ ወጥተው ራሱን የቻለ ኢትቢራ ሊመሰረት የቻለው። የቤተክርስቲያኑ ክልል በምስራቅ በኩል ከነዋሪው ከኤርደዶ ባዴ በምእራብ በዶሬ ሃብቴ በሰሜንና በደቡብ ሁለት ወንዞች አሉት ባጣቃላይ ከአንድ ሺህ በላይ አባላት አሉኣት። በመጀመሪያ ሲቋቋም ግን በጣም ጥቂት ሰዎች እንቅስቃሴ ነበር የተቋቋመው።

በእለቱ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ሰዎች፦

•ደንታሙ ኃብቴ 
•ደሳለኝ አበበ
•በዛብህ ሰዎሬ
•ኦሰቦ ፍሪሶ
•ኤርጎጎ ጮጫቶ
•ኤርጡሞ ደምሴ... ሌሎችም ብዙ ሰዎች በጎናችሁ ነን በማለት የሚያስፈልገውን ወጪ እያወጡ በገንዘብም በጉልበትም ባላቸው አቅም ሁሉ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ያደረጉ ብዙዎች አሉ።

እልፊኝ ያላቸው ሰዎች በየእልፊኞቻቸው ማረፊያ እያዘገጁ የሚያስፈልጉ የቁሳቁስ በማሟላት አያሌ ጊዜያትን አሳልፏልሉ።

♥የኢትቢራ ቤተክርስቲያን የህብረተሰቡን የፍቅር መንገድ አሳይታለች

ኡትቢራ የነበረው ፦ለትምህርት ቤት መቋቋም፤ ለገበያ መቋቋም ምክኒያት ሆናለች።

በአሁኑ ሰኣት ኢትቢራ ቤተክርስትያን የተለያዩ ቤሔራዊ ወንጌላውያንን በመላክ የመንግስቱን ቃል በማደረስ ላይ ትገኛለች።

በርከት ያሉ "ልጆቿም" በባህር ማዶ በስራ ምክኒያት ተበትነው እየኖሩ ነው። ለያንዳዱም በየእለቱ በጸሎት እና በጾም እየተማጸነች ትገኛለች።