የአዲስ ቅዳም ከተማ አመሰራረት አጭር ታሪክ አዲስ ቅዳም በድሮው ጎጃም አጠቃላይ ግዛት አገው ምድር አውራጃ ፣በባንጃ ወረዳ፣በባንጃ ለኮማ ምክትል ወረዳነት ከ1936-1987 ዓ.ም የቆየች ስትሆን ከ1987 ዓ.ም ወዲህ አዊ ብሔረሰብ ዞን ራሱን ችሎ ሲቋቋም ወረዳዎች ውስጥ የፋግታ ለኮማ ወረዳ ዋና ከተማ ነች ፡፡ አንዳንድ አፈታሪኮች ለኮማ የባንጃ ልጅ ሲሆን ፋግታ ደግሞ የአንከሻ ልጅ ነው ይላሉ ፡፡ከተማዋ ከመዲናችን አዲስ አበባ 470 ኪ.ሜ ፣ከክልሉ ርዕሰ ከተማ ባህርዳር 104 ኪ.ሜ እንዲሁም ከብሔስብ ዞን ርዕሰ ከተማ እንጅባራ 18 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ከአዲስ አበባ -ጎንደር በሚወስደው አገር አቋራጭ መንገድ ግራና ቀኝ ደጋማ ቦታ ላይ የተመሰረተች ናት ፡፡ሰባቱ የአገው አባቶች ዛሬ አዲስ ቅዳም እየተባለ የሚጠራውን ቦታ በድሮ ጊዜ “አጂስ ክዳሜ” ብለው ሰይመውት ቅዳሜ ቀን ለመወያያትና ለገቢያ ማዕከልነት(ኩሰጝፂ፣ዙሚትጝፂ፣ እንክርጝፂ ኧኧኮ) ይጠቀሙበት እንደነበር የአካባቢው ቀደምት አባቶችና አፈ ታሪኮች ያስረዳሉ ፡፡ በ1903 ዓ.ም ጎጃም ገዥ የነበረው ንጉስ ተ/ሃይማኖት ሲሞት በጊዜው የነበሩት የኢትዮጵያ ንጉስ አፄ ምኒልክ ጎጃምን ምስራቅ ፣ዳሞትና አገው ምድር ብለው ሲከፋፍሉ ለእነዚህ ግዛቶችም አስተዳዳሪ/ገዢ/ ሲመርጡ ራስ መንገሻ አቲከም አገው ምድርንና ደሞትን ገዢ ሆነው ተሾሙ፡፡ ከዚያ በፊት የነሩበት አዛዥ ገዛኻኝ ከወሰኑት ቦታ ባንግ ታራራ(አመዳይ ደን) ላይ ሆነው የጥንቱን ገበያ ስባቱ አባቶች ካስቀመጡት አንስተው ወደ አቅራቢያቸው አዛማች ኪዳነ ምህረት ወደ “ጉቢቺሊ” በመውሰዳቸው በመሰራቾቹ ተቃውሞ ብዙም ሳይቆይ ተመልሶ አሁን ካለንበት ከጥንቱ ቦታ ገበያው ተቋቁሟል ፡፡ ወደ ቦታው ሲመለሱ ግን የድሮ መጠሪያ “አጂስ ቅዳሜ” በመቀየር አዲስ ቅዳም ተብሎ ተጠርቷል ፡፡ ይህም ሊሆን የቻለው የአውጚ ቋንቋ በአማረኛ እየተወረስ በመሄዱ ነው ይላሉ አባቶች ፡፡

             የአዲስ ቅዳም ጦርነት

የኢጣሊያን ጦርነት ሽንፈት በኃላ በኢትዮጵያ አርበኞች ላይ ለመቀበል ከ40 አመታት በኋላ እደገትና ተነሳስተው ክብራቸውንም ለማስጠበቅ ኢትዮጵያ ላይ በኦጋዴን አካባቢ ድንበር ጥስው በመግባት አደጋን አድርሰዋል ፡፡ምንም እንኳ ያስቡት ባይሳካለቸውም የኢትዮጵያ አርበኞች ተጋድሏቸውን በየጫካውና በየሽንተረሩ ተያይዘውታል ፡፡ ለአምስት አመታት ያህል ከተካሄዱ ጦርቶች መካከል በድሮው አገው ምድር አውራጃ በአሁኑ አዊ አስ/ዞን ውስጥ አንዱ በጦርነት የአዲስ ቅዳም ጦርነት ነበር፡፡ ይህ ጦርነት የተካሄደው የኢጣሊያን የዳፈጣ ጦር ግንቦት 24/1932 ዓ.ም በሁለት አቅጣጫ ማለትም የእንጅባራው በደቡብና የዳንግላው በስተ ሰሜን የእንጅባራው አድጓሚ ተራራ እንዲሁም የዳንግላው ከአ/ቅዳም 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ላይ መትረይስ በመቀየስ ለገበያ የመጣውን ህዝብ ለመጨፍጨፍ ሲዘጋጅ ጀግኖች የአገው ምድር አባት አርበኞች የተለመደ ሽንፈት አከናንበው መልሰውታል ፡፡ አዲሲቅዳም ከተማ ምንም አይነት ቤት ስላልነበረው ቅዳሜ ቀን ለገቢያ ብዙ ህዝብ ይሰብሰብ ነበር፡፡ይህን ህዝብ ለመጨፍጨፍ ነበር የጣሊያን ፋሽስት ጦር ቋምጦ የተነሳው በዕለቱም ህዝብ በቦታው የተለያዩ መሳሪያዎችን ለመሸጥና ለመግዛት የመጡ የአገውምድር አባትአርበኞች፣ራስ ቢትወደድ መንገሻ ጀንበሬ፣ ፊታውራሪ የኔው አባዲት፣ ፊትአውራሪ ደስታወርቄ፣ቀኝ አዝማች በቀለ ወንድምና ቀኝ አዝማች አባ ደስታ የተሳተፉ ሲሆን በተለይ እና ፊት አውራሪ የኔው አባዲና ከማሳው በመመስግ ፣ራስ ቢትወደድ መንገሻ ጀንበሬ ከኳሽኒ መሽገው የፋሺስት ነጭ ደጋአመድ አድርገዋል፡፡ ጦርነቱ ከዕለቱ በግምት 4 ስዓት የተጀመረው ቀኑን ሙሉ ውሎ ጽሀይ ግባት ላይ በአገውምድር አርበኞች ድልአድራጊት ተፈፅሟል፡፡በዕለቱ በዱርገ ደሉ የነበሩ ሴቶች ፊታውራሪ ተብለው የተሸለሙ ሲሆን ከጣላትም ሆነ ከአባት አርበኞች የሞተ እንዳለ ሆኖ ብዙ መሳሪያዎችን ማለትም 500 ያህል አልቢን ምኒሽር ፣50 ሽጉጦች ፣8 የእጅ መትረይስ ከጠላት እጅ ተማርከዋል፡፡በማለት በወቅቱ ተሳታፊ የነበሩት አባት አርበኞች በትውስት ይናገራሉ ፡፡ የከተማዋ ገበሬዎች የአዲስ ቅዳም ከተማን ጥንታዊ የገቢያ ማዕከልነት ሲገልፁት በጃን ሆይ ጊዜ አዲስ ቅዳሜ ቀን የገቢያ ማዕከል በመሆንዋ ሀይለኛ የሆነ የገቢያ ምርት የገቢያ ግብዓት ለነበራትየዳንግላ ገበያን ቅዳሜ ቀን በተመሳሳይ ይውል ስለነበር ዳንግላ የገበያ ግብአት በመቀነሱ ወደ ረዕቡ ቀን እንደቀየሩ በጊዜው የነበረው ታሪክ አዋቂ አውራጃ ገዥ ግራ አዝማች አየሁ ጀንበሬያስረዳሉ ሆኖም ግን የደርግ መንግስት ከገባ በኃላ የገብያተኛውን የስራ ቀን እንዲውል ማለትም ቅዳሜ በማህበረሰዱ ዘምድ ስንበት ውይምሀጥማኖታዊ በዓል ተብሎ ስለሚከበር ነው ፡፡ ይህ አዲስ ቅዳም የገበያ ማዕከል በትልቅ ሾላ ዛፍ ስራ ስለነበር በዚህ ጥላ በመጠለል ጠላ፣ አረቄ፣ዳቦና የተለያዩ ነገሮች በተጨማሪ ይሸጥበት እንደነበር ይነገራሉ ፡፡ ገበያው ሰፊና ጥንታዊ በመሆኑ እንስሳት፣ እህል፣ማር፣ቅቤ ፣ሸቀጣ ሸቀጥ ፣ቡናና ሌሎችም ይገበያዩበታል ፡፡ የከተማው አመሰራረት ከተማዋ የተመሰረተችው በሁለት አጥቢያ ዳኛ በሚተዳደር የሽንኩሪ ሚካኤል እና በዚምብሪ ኪዳነ ምህረት ባለአባቶች መሬት ሲሆን ይህቦታ 1936 በፊት የባለአባቶች መሬት እንጂ ምንም አይነት ቤቶች ያልነበሩበት ፣ለከማነትም ያልታቀደ አልፎ አልፎ ቆባ ዛፍ ያለበት እንዲሁም ገበያተኛው የሚገበያይበት ትልቅ የሾላ ዛፍ እንደነበር የቦታው ነዋሪ አባቶች ያስተውሳሉ፡፡ ከጣሊያን ሽንፈት ወረራ በኃላ ፣ጃንሆይ ከውጭ ሀገር ከተመለሱ በኃላ /ማለትም 1936 ዓ.ም/ የአዲስ ቅዳም ከተማ ለገበያ ቦታ ሰፋትና ድምቀት በማመን በወቅቱ የነበሩ አገው ምድር አውራጃ አስተዳዳሪ ደጅ አዝማች ያረጋል እረታ ሰብሳቢነት ፣ በባንጃ ወረዳ አስረዳዳሪ ቀኝ አዝማች ቸኮል ጀንበሬ ፣በለኮማ ባንጃ ምክትል አስተዳዳሪነት ፣በፊት አውራሪ ደስታ ወርቄ በተገኙበት ገበያ ቦታ በአካባቢው ህዝብና የመሬት ባለይዞታዎች ፈቃደኝነት የገቢያው ስፋት በመከለሉ ከዚያው በመነሳት ምክትል አስተዳደሩና ወረዳ ቤተ ክህነት እንዲሆነ ተወሰነ፡፡ በ1951 በገቢያው ዙሪያ በአካባቢው ቤት በሰረቱት ከተማዋ መቆርቆር ጀመረች ከዚያ በፊት ለምክትል ወረዳ እናቤተ ክህነት ቢሮ በስተቀር ምንም አይነት ቤት ያልነበረ ሲሆን ከ1951 ጀምሮ ግንወ/ሮ የዝብነሽ ታመነ የተባለች ሴት የመሸታ መሸጫ የዳስ ጎጆ በጊዜው ከነበሩ መሬት ባለአባቶች ጠይቃ ስራች ፡፡ በኋላም እና ወ/ሮ ቦጌ ብዙነህ፣ነጋድራስ ቢረስ፣ አቶ አያሌው ፈንቴ እና ሌሎችም የመሬት ባለአባቶችና ሌላ አካባቢ የመጡ ከባለአባቶች መሬት እየገዙ የሳር ጎጆዎችን መስራት ጀመሩ፡፡ ነጋድራስ ቢረስ ወርቅነህ የከተማዋ ቆርቆሮ ነጋዴ ነበሩ ሲሆን ከአዲስ አበባ በበቅሎ በመጫን አምጥተው ከተማዋን ከሳር ቤት ወደ ቆርቆሮ ቤት በመቀየር ከተማዋም ከገጠር ወደ ከተማ በሚደረገው የነጋዴዎችና ሴተኛ አዳሪዎች ፍልሰት እየሰፋች መምጣቷን የከተማዋ ነዋሪዎች ያበስራሉ ፡፡ ወ/ሮ የዝብነሽ ታመነ የመጀመሪያ መሽታ ቤት/ጠላ እና አረቄ / ስትከፍት ወ/ሮ ቦጌ ብዙነሽ መጀመሪያ ከተማ ጠጅ ቤት እንደነበራቸው አባቶች ያወሳሉ ፡፡ መጀመሪያው ሰፈር የዶሮ ማነቂያ ሰፈር ይባላል ፡፡ ስያሜ የተሰጠውም ትንሽ አጣብቂኝ መንገድ ዛሬ ቴሌ ከመሰራቱ በፊት እንደነበር የሰፈሩ ነዋሪዎች ይናገራሉ፡፡ ( ምንጭ፡- ፋግታ ለኮማ ወረዳ ባህልናቱሪዝም ጽ/ቤት )