አዮሊስ ወይም አዮሊያ (ግሪክኛ፡- Αιολίς, Αιολία) በጥንት ምዕራብ አናቶሊያ (የአሁኑ ቱርክ አገር) በኤጊያን ባህር ላይ የተገኘ አውራጃ ነበረ።
አዮሊስ አውራጃ ደግሞ የሚስያ ክፍል ተባለች። ከ800 ዓክልበ. በፊት ግሪኮች (የአዮልያውያን ነገድ) 12 ነፃ ከተሞች ነበሯቸውና አብረው «የአዮልያውያን ማህበር» ሆኑ።