አዝማሪ ቋንቋ የሚሰኘው አዝማሪወች እርስ በርሳቸው የሚግባቡበትና ሌሎችን የሚያገሉበት የምስጢር ቋንቋ ነው። ይህን የሚያደርጉት ፡

  1. የአንድን ቃል ፊደላት በመቀየር
  2. ፊደላትን በመደጋገም
  3. አዲስ ፊደል ቃሉ ውስጥ በመጨመር
  4. የቃላቱን አናባቢወች ሙሉ በሙሉ በመገልበጥ
  5. የቃላቱን አናባቢወች በተለያየ መልኩ (2-3-1 ወይም 3-2-1 ወይም 1-3-2 በመገልበጥ)

ምሳሌ፡

ፊደል በመድገም ለማስተካከል

እንባ --> አናንባ

ደስ አለኝ --> ደሰሰና ሞሰኝ

ሳር --> ስርንስር

ፍሬ --> ፍርንፍር

ፊደል በመጨመር ለማስተካከል

ቀዳ --> ቀረዳ

በለጠ --> በለነጠ

አናባቢ ሙሉ በሙሉ በመገልበጥ ለማስተካከል

በላ --> ላበ

ተዝናና --> ናናዝተ

አናባቢ በለያየ መልኩ በማገላበጥ ለማስተካከል

ተኛ --> ኘታ

መብት --> ተምብ (3-1-2)

ወደቀ --> ደወቀ (2-1-3)

[1]

ማጣቀሻ ለማስተካከል

  1. ^ Wolf Leslau, An Ethiopian Minstrels' Argot, Journal of the American Oriental Society Vol. 72, No. 3 (Jul. - Sep., 1952), pp. 102-109