አዜብ መስፍን

የኢትዮጵያ 2ኛ ቀዳማዊት እመቤት

ወ/ሮ አዜብ መስፍን የህወሃት ነባር ታጋይና የኢትዮጵያው ጠ/ሚኒስትር የአቶ መለስ ዜናዊ ባለቤት ናቸው። ቀዳማዊ እመቤት በነበሩበት ወቅት በኢትዮጵያ ከፍተኛ የንግድ እንቅስቃሴ የሚያደርጉ ተቋሞች ስብስብ የሆነውን የትግራይ መልሶ ማቋቋሚያ ማህበር (ት.እ.ም.ት) መሪ ነበሩ፡፡ በአዲስ አበባ እና በሰሜን አሜሪካ የሚገኙ የኢትዮጵያውያን ሚዲያዎች ወይዘሮዋን በተለያዩ ከባድ የሙስና ቅሌቶች ይፈርጁዋቿል፡፡ ወይዘሮ አዜብ የባለቤታቸው መታሰቢያ የመለስ ዜናዊ ፋውንዴሽን መስራች እና የቦርድ ሰብሳቢ ናቸው፡፡

መለስ ዜናዊ ጋር ትዳር ከመመስረታቸው በፊት የአርከበ እቁባይ የፍቅር ጓደኛ እንደነበሩ የህዋህት ታጋይ የነበሩት ገብረመድህን አርአያ መስክረዋል።