አውቶስቴሮግራም ማለቱ ያለ መነጽር ከሁለት ቅጥ ገጽታ ላይ የተሳለን ስዕል ሦስት ቅጥ እንዳለው ሆኖ በሰው ልጅ አንጎል መታየቱ።

በነጠብጣብ የተሰራ ኦቶ ስቴሪዮግራም ሲሆን ፣ #አውቶስቴሪዮግራምን ማያ ስልት በመጠቀም ሲታይ፣ ስዕሉ ላይ 3 ቅጥ አሳ እንዳለ እንገነዘባለን

አውቶስቴሪዮግራምን ማያ ስልት ለማስተካከል

አውቶስቴሪዮግራምን ለማየት 3 ስልቶች መከተል ይቻላል።

አንድ፣ አፍንጫ የስዕሉን ገጽ እንዲነካ አድርጎ መጠጋት። ከዚያ አይንን ሳያንቀሳቅሱ ቀስ ብሎ ራቅ ማለት። በዚህ ወቅት አይን ስዕሉ ላይ ለማተኮር ስለሚፈልግ እንዳያታኩር፣ እንዲያውም ድሮ በነበረበት ሁኔታ እንዲቀጥል ማድረግ። ቀስ ብሎ ወደኋላ ሲኬድ የሆነ ቦታ ላይ 3 ቅጡ ምስል ይገለጣል።

ሁለተኛው ዘዴ ስዕሉን እየተመለከቱ ግን ከስዕሉ በስተጀርባ ላይ ባለ እቃ ላይ አይንን ማተኮር (በእርግጥ ሳይሆን፣ በምናብ)። ወይም በስዕሉ ውስጥ የራስን ነጸብራቅ ለማየት መሞከር።

ሦስተኛው እና የበለጠ አስተማማኙ መንገድ፣ አንድ ጣትን በአይንመካከል በማስቀመጥ፣ እዚያ ጣት ላይ በማተኮር፣ ቀስ በቀስ ጣቱን ወደስዕሉ በማስጠጋትና ጣቱ ላይ ምንጊዜም ትኩረት በማድረግ፣ ልክ 3 ቅጥ የሆነውን የአውቶ ስቴሪዮግራም ምስል ሲያዩ በማቆም ነው።

 
ይህ ኦቶ ስቴሪዮግራም ምስላቱን በ3 ጥልቀት ጠለሎች ደርድሮ ያሳያል
 
ጥልቀቱ እንደ ፒክሴሉመበታተን መጠን ይለያያል
 
አንጎላችን እያንዳንዱን ነበር በራሱ የጥልቀት ጠለል ላይ የማስቀመጥ ኃይል አለው