አወ እና አይደለም
አወና አይደለም የአይምሮ ጨዋታ ሲሆን፣ አንድ ሰው እንደጠያቂ ይመደብና ሌሎቹን ሰወች "አዎ" እንዲሉ ይገፋፋል ማለት ነው። "አዎ" ያለው ሰው ከጨዋታ ውጭ ይሆናል ማለት ነው። ጠያቂው የፈለገውን ጥያቄ መጠየቅ ይችላል። ለምሳሌ፡ "ስንት ወንድሞች አሉህ?" ሊለው ይችላል። ተጠያቂው ሁለት ወንድም ካለው "ሁለት" ይላል። ጠያቂው "ሁለት ወንድሞች አሉህ?" ብሎ እንደማረጋገጥ አስመስሎ ይጠይቀዋል። እዚህ ጋር ነው እንግዲህ- ተጠያቂው "አዎ" ካለ ጉዱ ፈላ! ከጨዋታው ይወጣል። እንደምንም ብሎ "አሉኝ" ወይም "ሁለት!" ብሎ ወይም ሌላ ቃል በመጠቀም ማረጋገጥ አለበት እንጂ፡ በፍጹም "አዎ" ማለት የለበትም።
ጨዋታው ከማዝናናቱም በላይ፡ የፈለጉትን መርጦ መናገር እንጂ ተገፋፍቶ አለመናገርን ለማለማመድ ጠቃሚ ሳይሆን አይቀርም።
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |