አኩኩሉ
አኩኩሉ ወይም ድብብቆሽ ህጻናት የሚጫወቱት ጨዋታ ሲሆን ፈላጊ አይኑን ይጨፍንና «አኩኩሉ» እያለ ስፍራ ውን ይጣራል ከዚያም ተፈላጊወች «አልነጋም» በማለት እራሳቸውን ይደብቃሉ። ተደብቀው ካበቁ በኋላ «አልነጋም» ማለትን ያቋርጣሉ በዚህ ጊዜ ፈላጊ አይኑን ይገልጥና መፈለግ ይጀምራል። ከተደበቁት መጀመሪያ የተያዘው በተራው ፈላጊ ይሆንና ጨዋታው ይቀጥላል። ነገር ግን ተደባቂወቹ በሙሉ ፈላጊን አምልጠው ሳይያዙ ማሪያምን ከነኩ ፈላጊ አሁንም ፈላጊ ይሆና ጨዋታው ይደገማል ማለት ነው።
ሌላኛው አይነት የዚህ ጨዋታ ምንድን ነው፣ ፈላጊ እስከተወሰነ ቁጥር እንዲጠራ ይደረጋል። ለምሳሌ እስከ 50 ጮክ ብሎ እንዲጠራ ይሆናል፣ በዚህ ጊዜ ውስጥ ተፈላጊወች እራሳቸውን ይደብቃሉ። ከዚያ ፈላጊ አይኑን ይገልጥና መፈለግ ይጀምራል። ከዚህ ውጭ ከላይ የተገለጸው ጨዋታና ይሄ አንድ አይነት ናቸው።
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |