ጥሬ ዕቃ ለ10 ደቂቃ ብቻ የተቀቀሉ 2 ራስ ድንቾች (ልጦ በሦስት መአዘን መክተፍ) 4 ካሮቶች (በክብ መክተፍ) 1 ራስ አበባ ጐመን (የአበባው ቅርጽ ተጠብቆ መክተፍ) 4 ዝኩኒዎች (በክብ መክተፍ) 1 የሾርባ ማንኪያ ኦሊቭ ኦይል (ሌላ አይነት ዘይት መጠቀም ይቻላል) 1 ሲኒ መሽሩም (ሊበላ የሚችል እንጉዳይ) ጨው ደርቆ ለሾርባነት የተዘጋጀ አትክልት (ክኖር የደረቀ አትክልት)

አሠራር 1. በ400 ዲግሪ ፋራናይት ወይም በ205 ድግሪ ሴሊሽየስ ኦቭን የምግብ ማብሰያውን ማሞቅ፡፡ ከዚያም ማብሰያ ትሪውን (ፓትራ) ዘይት ወይም የዳቦ ቅቤ መለቅለቅ፡፡ 2. ማብሰያው ትሪ ላይ አትክልቱን በሙሉ አቀላቅሎ በደንብ እስኪርስ ድረስ ዘይት መለቅለቅ፡፡ ለሾርባነት የተዘጋጀውን (ደርቆ የታሸገውን አትክልት) ነስንሶ ኦቮን ውስጥ መክተት እና አትክልቶቹን ከ30-45 ደቂቃ ማብሰል፡፡ (ኦቭን ካልተገኘ ጐድጐድ ባለ መጥበሻ ወይም ብረት ድስት አትክልቱን ማብሰል ይቻላል) በዚህ መልኩ የተዘጋጀ ምግብ 4 ሰዎችን ይመግባል፡፡