አብድ አል ሻኩር ኢብኑ ዩሱፍ

ለማስተካከል

አብዱልሻኩር ኢብን ዩሱፍ የሐረር አሚር ነበር (1783-1794)። ለአጎራባች ኦሮሞ ስጦታ የሰጠ የመጀመሪያው የሐረር አሚር ነበር። በመጀመሪያዎቹ የንግሥና ዓመታት ወደ አጎራባች ኦሮሞ አካባቢ በሄደበት ጊዜ ለጃርሶ እና ለኖሌ ኦሮሞዎች የሚገለገሉበትን የአንሶላ ንጣፎችን በስጦታ መልክ አቅርቦላቸው ነበር፡፡ ይህን ያደረገው ለጨው እና ለሌሎች ሸቀጦች በግዛታቸው እንዲገቡ መንገድ ለማስለቀቅ ሊሆን እንደሚችል ይታመናል።[1]

አብድ አል ሻኩር ኢብኑ ዩሱፍ

أمير عبد الشكور بن يوسف

11ኛው የሀረር አሚር

አብደላህ II ኢብኑ አሊ አብድ አሽ-ሻ
ግዛት: 1783–1794
ቀዳሚ: መሀመድ ኢብን ዩሱፍ
ተተኪ: አብዱልከሪም ኢብን ሙሐመድ
የተወለዱት ቀን : 1750s
የትውልድ ቦታ: ሐረር, የሐረር ኢሚሬትስ
የሞተበት ቀን: 1794
የሞተበት ቦታ: ሐረር, የሐረር ኢሚሬትስ
ሥርወ መንግሥት: የዳዉድ ሥርወ መንግሥት
ሃይማኖት: የሱኒ እስልምና

ሌላው ኦሮሞን "ለማሰልጠን" ያደረገው ጥረት ሲሆን እነደ አንድ ምሳሌ ለመጥቀስ  ለባግዳዲው ቅዱስ አብዱልቃድር አል-ጂላኒ በሼህ ሁሴን መቃብር አቅራቢያ በደቡብ በኩል በኦሮሞ ህዝብ ግዛት ውስጥ የሚገኘውን ቤተመቅደስ ገነባ። [2] አሚር አል ሻኩር የሲጂል እና የዲዋን ተቋማትን እንደገና በማስተዋወቅ የሀረርን አስተዳደራዊ ስርዓት ለማሻሻል ያደረገው ሙከራ በ1785/6 ዓ.ም በተጻፈ ሰነድ ላይ ተረጋግጧል።[3]

  1. ^ Caulk, R. A. (1977). "Harär Town and Its Neighbours in the Nineteenth Century". The Journal of African History 18 (3): 369–386. ISSN 0021-8537. https://www.jstor.org/stable/180638. 
  2. ^ J. Spencer, Trimingham (1952). Islam in Ethiopia. Oxford: Geoffrey Cumberlege for the University Press,. pp. 253-256. 
  3. ^ WAGNER, EWALD (1974). "Three Arabic Documents on the History of Harar". Journal of Ethiopian Studies 12 (1): 213–224. ISSN 0304-2243. https://www.jstor.org/stable/44324707.