አብዛኛው የሐይቁ ክፍል በጎንደር ሲገኝ ቀሪው ደግሞ በጎጃም ይገኛል፡፡

መለጠፊያ:ጎጃም በሰሜን ምራብ ኢትዮጵያ የሚገኝና በአባይ ወንዝ ተከቦ የሚገኝ ባህር ዳርን ፍኖተ ሰላምን አገው ምድርን መተከልን ፓዊ ቆላ-ደጋዳሞትን፣ አቸፈርን ደብረ ማርቆስን ሞጣና ብቸና አውርጃዎች እና በነዚ ውስጥም ከ 35 በላይ ወረዳዎችን ይዞ የሚገኝ የራሱ ስርዎ መንግሥት የነበረው ከፍለ-ሃገር ነው። ጎጃም ውስጥ ኣሉ ከሚባሉት ከተሞች እንደ ባሕር ዳር ፡ ደብረ ማርቆስ ፡ፍኖተ ሰላም ፡ቡሬ ፡ኮሶበር ፡ ዳንግላ ፡ቻግኒ ፡ ኣዴት ፡ መራዊ ፡ ሞጣ፡ ቢቸና፡ ደጀን ይገኙበታል ፡፡ ጎጃም እንደነ በላይ ዘለቀ ያሉ ጀግኖች መፈጠሪያ እንዲሁም የ ኣባይ እና የጣና ባለቤት ናት ፡፡

ጎጃም የቅኔ ትምህርት በስፋት የሚሰጥበት ፡እንዲሁም እንደነ የፍቅር እስከ መቃብር ደራሲ ሀዲስ አለማየሁ (ዶ ር) (1902- 1996 )ኣ.ም ኣቤ ጉበኛ (1925 - 1972 )ኣ.ም ዮፍታሄ ንጉሤ(1897-1937 ) ኣ.ም የመሳሰሉ የጥበብ ሰወችን ኣፍርታለች ፡፡ ጎጃም በጤፍ አምራችነት ከታወቁት የኢትዮጵያ ክልሎች ቀዳሚውን ስፍራ ይይዛል። በተለይ የአዴት ጤፍ በባህር ዳር ጎንደር ደሴ እና መቀሌ ነዋሪዎች ዘንድ በስፋት የታወቀ እና ተወዳጅም ነው። እንዲሁም በምስራቅ ጎጃም እነብሴ ሞጣ ዙሪያ ወይንውሀ እና ጎንቻ ሲሶ ግንደወይን ዙሪያ የሚመረተው ጤፍ የአዲስ አበባን ህዝብ ገትሮ እንደያዘ ይነገራል።ቡሬ ዙሪያ የሚበቅለው በርበሬ በቆሎ ደግሞ የመላው የኢቲዮጵያን ህዝብ ገትሮ እንደያዘም ይነገርለታል፡፡ በነገራችን ላይ ቡሬ ዙሪያ ይህንን ብቻ አይደለም የሚያበቅል እንደ ጤፍ፣ሽንብራ፣ቦለቄ፣ዳጉሳ፣መጥቀስ ሆነብን እንጂ የማይበቅል ነገር የለም፡፡በዋናነትም ከ ቡሬ ዙሪያ ወረዳ ገዳም ልጃሞር ቀበሌ ይህንን በማምረት ይጠቀሳል፡፡ ጎጃም ሌሎች እንደ ገብስ ስንዴ በቆሎ ባቄላ አተር ወዘተ የሰብል አይነቶችን በማምረትም ይታወቃል። ጎጃም የአባይ እና ሌሎች የበርካታ ወንዞች መነሻ ነው ።ጮቄ ተራራ በዚሁ ክፍለ ሃገር ይገኛል።ጎጃም በኣሁኑ ጊዜ ማለትም ኣገራችን የፌደራሊዝም ስርኣት ከተከተለች ወዲህ ከኣራት ኣስተዳደር ዞን ተከፍሏል ።ሥወስቱ ማለትም አዊ፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ጎጃም በአማራ ክልል ሲገኙ መተከል ቤሻንጉል ጉምዝ ክልል ተካቷል ።