አብርሃም ዮሴፍ በ1985 ግንቦት 28ቀን ለእለተ ሰኞ አጥቢያ ከሌሊቱ በዘጠኝ ሰዐት በደብረማርቆስ ከተማ ተወለደ። ወላጅ እናቱ ንፁህ አየለ ወላጅ አባቱ ዮሴፍ ስብሐቱ ይባላሉ። በትምህርት አለም - አንደኛና ሁለተኛ ክፍልን በደብረ ማርቆስና ፍኖተ ሰላም ከተማ በሚከገኙ ትምህርት ቤቶች ተማረ። ከ1994 ጀምሮ በአዲስ አበባ በሚገኘው አሳይ የሕዝብ ትምህርት ቤት አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን አጠናቀቀ። ለፍልስፍና ትምህርት ልዩ ትኩረትና ፍቅር የነበረው አብርሃም አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ያለፍላጎቱ የተመደበበትን የፖለቲካል ሳይንስ ጥናት ዘርፍ ከስድስት ወር በላይ ሊታገስ ባለመቻሉ በ2005ዓ.ም አቋርጦ ወጣ። በነበረው ልዩ የስነ ፅሁፍ ችሎታና የቋንቋ ብቃት በ2003 ዓ.ም የአስራ አንደኛ ክፍል ተማሪ ሳለ በሪፖርተር ጋዜጣ ላይ በቋሚነት ደላላውና ታክሲው በሚባሉ አምዶች ላይ ለስምንት አመት የመፃፍ እድሉን አግኝቷል። ዳዊትን አያርገኝ በሚል ርዕስ በ2002ዓ.ም አዘጋጅቶ በድምፅና ሙዚቃ የተቀናበረ ስራውን አቅርቧል። በዋናነት የሚፅፈው አጭር ልብወለድ ነው። https://www.youtube.com/watch?v=PIKGwpX6yHE&pbjreload=101