አብርሃማዊ ሃይማኖቶች የሚባሉት እስልምና ክርስትና እና አይሁድ ናቸው የእነዚህ ሃይማኖቶች ዝንባሌ ስርዓተ ቀብር ነው ሃይማኖቱ በመገለጥ ላይ የተመሰረተ ሃይማኖት ሲሆን ሰው ከሞተ በኋላ ይነሳል ብለው ያምናሉ ቅዱስ ምልክታቸው መስቀል ግማሽ ጨረቃ ከ ባለአምስት ኮከብ ጋር እና ስድስት ጫፍ ያለው የዳዊት ኮከብ ነው የአምልኮ ስፍራቸው አብያተ ክርስቲያናት መስጂድ እና ምኩራብ ነው የጸሎት ስነ ስርዓታቸው ሳላህ አሚዳህ እና ቅዳሴ ነው በዕለት 5፣3 እና 7 ጊዜ መጸለይ የሃይማኖቱ ስርዓት ነው ቅዱስ መጽሃፋቸው መጽሃፍ ቅዱስ ታናክ ቶራህ እና ቁርዓን ነው ቅዱስ ስፍራቸው እየሩሳሌም ቫቲካን መካ መዲና እና ቤተልሄም ናቸው ቃል የተገባላቸው ምድር መንግስተ ሰማያት ኦለም ሃባ እና ጀነት ናቸው የቅጣት ስፍራቸው ጌሄና ገሃነመ እሳት እና ጀሃነም ናቸው አብርሃማዊ ሃይማኖቶች የተባሉበትም ሶስቱም ሃይማኖቶች አብርሃም አባታችን ብለው ስለሚያምኑ ነው ዋነኛው ክብረ በዓላቸው ኢድ አል አድሃ ኢድ አል ፊጥር ሀኑናክ ዮም ኪፑር ልደተ ክርስቶስ እና ትንሳዔ ይጠቀሳሉ [1]

  1. ^ Adel Theodor Khoury: Abrahamitische Religionen. In: Religion in Geschichte und Gegenwart (RGG)4. Band 1. Tübingen 1998, S. 78, doi:10.1163/2405-8262_rgg4_SIM_00084 (Zugang kostenpflichtig).