አባ ዶዮ ዋሚገሮ የኦሮሞ ባላባት፣ የኢትዮጵያ መጀመርያ ፓርላማ አባል፣እና አርበኛ ነበሩ።
በጣልያን ፋሺስቶች ወረራ ጊዜ የኢትዮጵያ ሕዝብን በየዘሩ ለማከፋፈል ሲሞክሩ፣ አባ ዶዮ ጤፍን ነጭ ከጥቁሩ እንዲለዩ ጠየቋቸው። ይህንን ባለመቻላቸው ታዲያ እኛ ሁሉ ከአማራ፣ ኦሮሞና ብዙ ሕዝቦች የተቀላቀለን ሆነን እኛን ማስለየት ከዚህ በላይ የማይቻል ነው ብለው መለሱዋቸው።