አባይ በለጠ
አባይ በለጠ ታዋቂ ኢትዮጵያዊ ድምፃዊ የነበረ ሲሆን ለስላሳ ወይም የትካዜ ዜማዎች በመጫወት ይታወቃል።[1]
የህይወት ታሪክ
ለማስተካከልአባይ በለጠ በ፲፱፻፶፬ ዓ.ም. አሪዞና የምሽት ክበብ ውስት በድምፃዊነት ተቀጥሮ ድምፁን ከሙዚቃ ጋር ሲያርቅ ከቆየ በኋላ በዚያው ዓመት በጦር ሠራዊት ክፍል በድምጻዊነት ተቀጥሮ ለ፲፱፻፶፭ ዓ.ም. መግቢያ እንቁጣጣሽ በዓል በመድረክ ላይ ወጥቶ በሕዝብ ፊት መጫወት ጀመረ። ሙዚቃን እንዲወድ በይበልጥ ስሜት ያደረበት እራሱ መጫወት ከጀመረ በኋላ እንደሆነ አባይ ይናገራል።[1]
የሥራዎች ዝርዝር
ለማስተካከልእስከ ፲፱፻፶፯ ዓ.ም. ድረስ ፲፫ ያህል ዜማዎችን ተጫውቷል። ከእነርሱም መካከል «የአዲስ አበባ ውበት»፣ «ምነው ብታስቢ» እና «ሳገኝ ከተፍ ያለች» የሚባሉት ይገኙበታል።[1]
ማጣቀሻ
ለማስተካከል- ^ ሀ ለ ሐ "ናሽናል ቢብሊዮግራፊ ቡድን፣ የአንጋፋ አርቲስቶች መዝገበ የሕይወት ታሪክ፣ መጋቢት ፳፻፣ ገጽ 31". Archived from the original on 2011-09-29. በ2010-12-18 የተወሰደ.