አቶ አባተ ኪሾ በሙስና ምክንያት ከስልጣን ወርደው በእሥር አራት ዓመት ያህል ካሳለፉ በኋላ በምህረት ከመለቃቀቸው በፊት ኢሕአዴግ ኢትዮጵያን ሲቆጣጠር በኢሕአዴግ ጥላ ሥር የሲዳማን ዴሞክራሲያዊ ድርጅትን በመመሥርታቸው የመጀመሪያው የደቡብ ኅብረት ዴሞክራሲያዊ ድርጅት/ደ.ኅ.ዴ.ድ. ጸሃፊና በኢሕአዴግ ዘመነ መንግሥት የመጀመሪያው የደቡብ ክልል ፕሬዚዳንት ነበሩ። አቶ አባተ የትምህርት ደረጃቸው በ1ኛ ደረጃ መምህርነት ኮርስ ከአዋሳ መህራን ማሰልጠኛ ተመርቀው የ5ኛ ክፍል ህብረተሰብ ሳይንስ አስተማሪ ነበሩ።