አበበ በሶ በላ።
ታሪክ
ለማስተካከል«አበበ በሶ በላ» ለመጀመሪያ ጊዜ በስፋት ጥቅም ላይ የዋለው በበ1970ዎቹ መሠረተ ትምህርት ዘመቻ ጊዜ ነበር። ከ«በ» ውጪ ከ«በ» ጋር የሚመሣሰሉ ሌሎች ሶስት ብቻ ፊደላትን የያዘ በመሆኑ ለማንበብ ይቀላል። «በ» ለመጻፍም ቢሆን በጣም ከሚቀሉት ፊደላት ስለሚቆጠር፣ ቀሪዎቹ ፊደላትም ከርሱ ጋር በጣም ስለሚመሳሰሉ ለመጻፍም ብዙ የማይከብድ ዓረፍተ ነገር ነው።
ተመሳሳይ
ለማስተካከልከዚሁ ጋር የሚመሣሰሉ ሌሎች ዓረፍተ ነገሮች፦
- ጫላ ጩቤ ጨበጠ። (በተለይ ጨ እና ጠ)
- ጨቡዴ ጣሳ አጠበ።