አሽጋባት (Aşgabat) የቱርክሜኒስታን ዋና ከተማ ነው።

አሽጋባት
Aşgabat/Ашгабат
ዋና ከተማ
አገር ቱርክሜኒስታን
የቦታ ስፋት
   • አጠቃላይ 440
ከፍታ 219
የሕዝብ ብዛት
   • አጠቃላይ 1,031,992
ድረ ገጽ ashgabat.gov.tm

የሚኖርበት የህዝብ ቁጥር 727,700 ሆኖ ይገመታል። ከተማው 37°58′ ሰሜን ኬክሮስ እና 58°24′ ምሥራቅ ኬንትሮስ ላይ ተቀምጦ ይገኛል።

የአሽጋባት ሥፍራ ከጥንታዊ ጳርቴ ሰዎች ዋና ከተማ (ከ260 እስከ 15 ዓክልበ. ገዳማ) ከኒሳ ፍርስራሽ ቅርብ (18 ኪሎሜትር) ነው። ያንጊዜ በሥፍራው ኮንጂካላ የተባለ መንደር ተገኘ፤ ይህም መንደር በ13ኛው ክፍለ ዘመን ዓ.ም. በሞንጎሎች ተጠፋ።

አሽጋባት አዲስ መንደር ሆኖ በ1810 ዓ.ም. በሩሳውያን ተመሠረተ። ስሙ ከፋርስኛ «የፍቅር ከተማ» እንደ መጣ ይታመናል። ከ1909 እስከ 1919 ዓ.ም. ስሙ በሶቭየቶች ፖልቶራትስክ ተባለ። ከ1919 እስከ 1983 ድረስ በሩስኛ አሽካባድ ተባለ።