አሸንድየ የአማርኛ ቃል ነው። በዚህ በዓል፣ ህጻናት አሸንዳ ከተባለ፣ የነጭ ሽንኩርት ቅጠል የሚመስል ረጅም ሳር የተለያዩ አይነት ጌጦችን በማበጀት፣ እንዲሁም ቀበቶና ቀሚስ በመስራት፣ በየቤቱ በመሄድ

አሸንድየ አሸንድ አበባ
እርግፍ እንደ ወለባ

እያሉ በመዝፈን የሚጨፍሩበት የጨዋታና በዓል አይነት ነው። አለቃ ታየ በ1902 ዓ.ም. በታተመ የትብብር መጽሐፋቸው፣ አሸንድየ በዓልን አሸንዳ በማለት በራሱ በተክሉ ስም ይጠሩታል[1]። ይህ በዓል፣ በእርሳቸው ዘመን በሚከተሉት የግጥም ስንኞች ይታጀብ ነበር፦


አሸንዳ በሉ
አሸንዳ
አሸንዳ ብዬ
አሸንዳ
ለባሌ ብዬ
አሸንዳ
ጎመን ቀቅዬ
አሸንዳ
አረ ኣረረብኝ
አሸንዳ
እናንተ ሆዬ
አሸንዳ በሉ
አሸንዳ


የበዓሉን አዋጭነት በሚያሳይ መልኩ፣ እንዲህ በማለት የዘመሩ ሕጻናት በሚያገኙት ገንዘብ ወይንም ፍሪዳ፣ ወይንም በግ፣ አለበለዚያ ጠላና እንጀር ይገዙ እንደነበር አለቃ ታየ አስፍረዋል።

  1. ^ Mittwoch, Eugen, 1876-1942. Abessinische Kinderspiele. Berlin: Gedruckt in der Reichsdruckerei, 1910.