አሱል
አሱል (ኮሪይኛ፦ 아술) በኮርያ ልማዳዊ አፈ ታሪክ በጥንታዊ ኮርያ (ጎጆሰን) የነገሠ ንጉሥ ወይም «ዳንጉን» ነበር። እርሱ ከዳንጉን ሰውሃን መንግሥት ቀጥሎ ገዛ።
በጠቅላላ ለ35 ዓመታት (ምናልባት 1770-1735 ዓክልበ.) እንደ ነገሠ ይጻፋል። ከዚያ በኋላ ኖዕል ተከተለው።
በ1903 ዓም. በኮሪይኛ የተዘጋጀው ዜና መዋዕል ኋንዳን ጎጊ ስለዚሁ አፈታሪካዊ ዘመን መረጃ ይሰጣል፤ ሆኖም በብዙ የኮርያ መምህሮች ዘንድ ይህ መጽሐፍ እንደ ትክክለኛ ታሪክ አይሆንም። አሱል ካደረጋቸው ሥራዎች መካከል ዋና ዋናዎቹ እንዲህ ናቸው፦
- 1769 ዓክልበ. ግ. - «ዳንጉን (አሱል) እንዲህ በጎ ነብር፤ ጠልና ዝናብ በፋንዲያ አገር ይሆናል እያለ ወንጀል ያለባቸውን ሰዎች ላይ ምንም ቅጣት አልፈረደም ነበር። ስለዚህ ስለ ዳንጉኑ ምግባር ወንጀለኞቹ በግብረ ገብ ተሻሻሉ። ስለዚህ አስተዋይነትና ትምህርቶች በብሔሩ ሁሉ ከዳንጉን ተስፋፉ። በዚያ ቀን ሁለት ፀሐዮች እንደ ገቡ መሰለ፣ ተመልካቾችም ስንደ ሰፊ አጥር ይምሰሉ ዘንድ።»
- 1768 ዓክልበ ግ. - የቸውንሄ አገረ ገዥ ዉቻክ አመጸና ቤተ መንግሥቱን ተዋጋ፤ አሱል ወደ ሳንቹን ሸሽቶ አዲስ ቤተ መንግሥት በጉዋል ተራራ ደቡብ ግርጌ አሠራ። ዳንጉን አለቆቹን ዉጂ እና ዉዩል አመጹን እንዲጨምቁ አዘዘና ዉቻክን ገደሉት። ከ፫ ዓመታት በኋላ አሱል ወደ ፊተኛው ዋና ከተማ መመልስ ቻለ።
- 1735 ዓክልበ. ግ. - አሱል ዓረፈና ከ፭ ሚንስትሮቹ አንዱ «ዉጋ» የተባለው ኖዕል ተከተለው።
ቀዳሚው ሰውሃን |
የጆሰን ዳንጉን | ተከታይ ኖዕል |