አሰግድ ግብረእግዚአብሄር
አሰግድ ገብረእግዚአብሔር በማስታወቂያ ሚኒስቴር በልዩ ልዩ ክፍሎች ሰርቷል በጋዜጠኛነትም የሰንደቃላማችን ጋዜጣ ምክትል አዘጋጅ እስከመሆን ደርሷል። በብሄራዊ ትያትር ቤትም የህዝብ ግንኙነት ክፍል ምክትል ሀላፊም ነበር።
እንደዛሬው የትያትር ጥበብ ሳይስፋፋ በቴሌቪዥን መስኮት ብቅ ከሚሉ ጥቂት ተዋናዮች መካከል አንዱ አሰግድ ነበር። አምስት ለዜሮ፣ ግደይ ግደይ አለኝ፣ ሳይቋጠር ሲተረተር፣ ብቀላና ሁለት ወዶ በተባሉት ተውኔቶች ላይ ተጫውቷል። ሀምሌትና በቀይ ካባ ስውር ደባ ደግሞ በመድረክ ላይ ከሰራቸው መካከል የሚጠቀሱ ናቸው። በዛን ዘመን በኢትዮጵያውያን አርቲስቶች ከተሰሩት የውጪ ፊልሞች ደግሞ ፈረንጅ በተባለው ፊልም ላይ ተሳትፎ ችሎታውን አስመስክሯል።