አርኖ ሚሼል ዳባዲ
አርኖ ሚሼል ዳባዲ ዳራስ (1815-1893) ፈረንሳዊ ሲሆን የኖረው በ19 ነኛው ክፍለ ዘመን ነበር፡፡ የ"በኢትዮጵያ ከፍተኛ ተራሮች ቆይታዬ" የተሰኘው መጽሐፍ ደራሲ ነው።
በተመራማሪነትና በጀብደኝነት ስሜት ተነሳስቶ ገና ጎረምሳ ሳለ ከታላቅ ወንድሙ ከአንቷን ቶምሰን ዳባዲ ዳራስ (1810-1897) ጋር ሆኖ እ ኤ አ በ1837 ዓም ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ መጣ።
እሱና ወንድሙ ወደ ኢትዮጵያ በተጓዙበት ወቅት ሀገሪቱ እውነተኛ ንጉሠ ነገሥት አጥታ የጉልበተኛ መሳፍንት መጫወቻ ሆና ነበር። በጎንደርና በዙሪያዋ ላይ ትንሹ ራስ ዐሊ የተባሉ የኦሮሞ መስፍን እናታቸውን ወይዘሮ መነንን ለአሻንጉሊት ወይም ለስም ንጉሠ ነገሥት ድረው እቴጌ አሰኝተው እሳቸው የበላይ ሆነው ይፈልጡ ይቆርጡ ነበር፡፡ በጎጃምና በትግራይ ደግሞ ደጃዝማች ጎሹና ውቤ ለይስሙላ ያህል ከራስ ወሊ የበታች ሆነው ያሻቸውን ያደርጉ ነበር። አርኖ ዳባዲ በትግራይ በኩል ወደ ኢትዮጵያ ገብቶ ከዚያም ወደ ጎጃምና ጎንደር ዘልቆ መንገድ ላይ የገጠመውን ዘርዝሮና በነዚህ መሬቶች ላይ የታዘበውን አብራርቶ በዚህ መጽሐፍ ውስጥ አኖረልን። ይህ ደራሲ ዓይኑና እእምሮው መራዥና ስል በመሆናቸው በዛን ዘመን ይታዩ የነበሩትን የኢትዮጵያውያንን ቁመና እለባበስ እኗኗርና ባህል ፍንትው እድርጎ - ስሏቸዋል። የጦርነታቸውን ስልትና ዘዴ እየተከታተለ ከትቦታል። ከላይ ከተጠቀሰው ሁሉ በላይ ግን እነዚህ ሥልጣን የጠማቸው መሳፍንት ሃይ የሚላቸው ንጉሠ ነገሥት ባለመኖሩ እርስ በርሳቸው እየተዋጉ ሕዝባቸውን ያወርሱ ነበር፡፡ የሁሉም ምኞትና ዓላማ ወኅኒ አምባ ከተባለው የልዑላን እራሳቸው በባለሙሉ ሥልጣን እንደራሴነት ኢትዮጵያን መግባት ነበር፡፡ አርኖ ዳባዲ ከነዚህ መሳፍንት መካከል ስመጥርና ገናና ከነበሩት ከደጃች ጎሹ ጋር ጥብቅ የሆነ ወዳጅነት መሥርቶ ነበር። አልፎ ተርፎም በተሳተፉባቸው አንዳንድ ጦርነቶች አብሮ ተዋግቷል። በዚያ ወቅት ያየውንና የሰማውን በዝርዝር ዘግቦታል፡፡ የኢትዮጵያ ዘመነ መሳፍንት መንፈስ በይበልጥ ለመረዳት የሚሻ ሰው ሁሉ ይህን መጽሐፍ ሲያነበው ይገባል። [1]
በአሥራ ዘጠነኛው ክፍለ ዘመን ወደ ኢትዮጵያ ከመጡ በርካታ የእውሮፓ ተጓዦችና ሀገር ጎብኝዎች መካክል አርኖ ዳባዲ አንዱ ነው፡፡ አርኖ ዳባዲወደ ሀገራችን የመጣው በታሪካችን ዘመነ መሳፍንት ተብሎ በሚጠራው ዘመን ነው፤ ይህ ፈረንሳዊ በሰሜን በሰሜን ምዕራብና በምዕራብ ኢትዮጵያ በቆየባቸው ዓመታት ውስጥ በዓይኑ ያየውን በዕለት ማስታወሻው እያስፈረ ከቆየ በኋላ በመጨረሻ በመጽሐፍ መልክ ለማሳተም በቅቷል፡፡ መጽሐፉ በአሥራ ዘጠነኛው ክፍለ ዘመን በሀገራችን የነበረውን ፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ ቁልጭ አድርጎ ያሳየናል፡፡ አርኖ ዳባዲ በተለይም በደጃች ውቤ ኃይለማርያም በራስ ወሊ አሉላ በደጃች ጎሹ ዘውዴ እና በልጃቸው በደጃች ብሩ ጎሹ እንዲሁም በጎንደር ቤተ መንግሥት በዓይኑ ያየውን በሥዕላዊ መንገድ ገልጦ ያስረናል፤፤ ወታደራዊ ዘመቻ የበዛበት የዘመነ መሳፍንት ውስብስብ ፖለቲካ ምን ይመስል እንደነበር በዓይነ ሕሊናችን እንድናየው ያደርገናል፡፡ ደጃች ብሩ ጎሹ ባደረጉት ዘመቻ እንደ አንድ ወታደር ሁ በመዝመት በዓይኑ ያየውን ይተርክልናል፡፡ ይህን መጽሐፍ የታሪክ ባለሙያዎች ብቻ ሳይሆኑ የሀገራቸውን ታሪክ ባሕልና አኗኗር ማወቅ የሚፈልጉ ዜጎች ሁሉ ሊያነቡት ይገባል። [2]
በዘመነ መሳፍንት የተፃፈ ግጥም ዳባዲን ያመለክታል። ከአሰፋ ብሪቱ ተገጠመ አገሯ የውሽ ደረቤ (ጐጃም)።[3] (በኢትዮጵያ የዳባዲ የመጀመሪያ ስም ሚካኤል ነበር።)
- እህል እንኳን የለኝ እንዳላቃምሰው
- እኔን እኔን ይብላኝ የራስ ሚካኤል ሰው።
- ተደጓሹን ይሆን ዓረቡ ቢያንሰው
- ሚካኤል ጐራዴ/ው/ አሽሟጣጭ የለው።
- እኔስ ብዬ ነበርሁ የውድማ መጣሻ
- ብር አፈሰሱበት በሚካኤል ጋሻ ።
ወደ ኢትዮጵያ ካደረገው ጉዞ በኋላ ወደ ፈረንሳይ ተመልሶ በ1864 አግብቶ 9 ልጆችን ወልዷል።
ቤተ መንግስት ገንብቶ ከቤተሰቦቹ ጋር ኖረ።
ይሁን እንጂ ቤተ መንግሥቱ ለሪል እስቴት ፕሮጀክት መንገድ ለማድረግ በ1985 ወድሟል።
ዋቢ መጻሕፍት
ለማስተካከል- ^ ዳባዲ, አርኖ ሚሼል. "በኢትዮጵያ ከፍተኛ ተራሮች ቆይታዬ" የተተረጎመው በ"ገነት አየለ" እና አስተያየት ሰጥተዋል ፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሳ.
- ^ ዳባዲ, አርኖ ሚሼል. "በኢትዮጵያ ከፍተኛ ተራሮች ቆይታዬ" የተተረጎመው በ"ገነት አየለ" እና "ፋንታሁን እየለ" አስተያየት ሰጥቷል.
- ^ Abebe, Berhanou (1987). "Distiques du Zamana asafent", Annales d'Éthiopie. p. 32-33. https://www.persee.fr/doc/ethio_0066-2127_1987_num_14_1_930?q=D%27Abbadie.