አራል ባሕርመካከለኛ እስያዑዝበኪስታንና ከካዛኪስታን መካከል የተገኘ ታላቅ ባሕር ወይም ሀይቅ ነበረ።

የአራል ባሕር መጠን ከ1952 ዓም እስከ 2006 ዓም ድረስ ሲቀነስና ሲጠፋ

ከጥንታዊ ዘመን ጀምሮ እስከ 1953 ዓም ድረስ፣ ይህ ሀይቅ ከዓለም ፬ኛው በስፋት ያለው ትልቅ ሀይቅ ነበረ። ከዚያ በኋላ ግን፣ የሶቭየት ኅብረት አለቆች ለበረሃ መስኖ ይሆናል በማባባል ወደ ሀይቁ የፈሰሱትን ወንዞች ከመንገዶቻቸው አዞሩ። ስለዚህ የሀይቁ መጠን ይቀነስና ይደረቅ ጀመር። ከ1999 ዓም በኋላ አንድ ሐይቅ ይኖራል ለማለት አልተቻለም፤ በአሁንም ሰዓት አንዳንድ ትንንሽ ሐይቆች ቀርተዋል፣ በአጠቃላይ ግን ዙሪያው ታላቅ ምድረ በዳ እና በረሃ ሆኗል።

የአራል ባሕር መጠን በ1981 እና በ2006 ዓም