አምባው ተሰበረ
አምባው ተሰበረ
(12)አለቃ ድንግላዊ መነኩሴ ነበሩ። በእነ አለቃ ዘመን ወይዛዝርት መነኩሴዎችን ካሳቱ ለነሱ ወይ ለቤተሰቦቻቸው የግብር ምህረት ይደረግላቸዋል አሉ። እንደጀግናም ይወደሳሉ። ሰለዚህ መነኩሴን ለማሳት እና ለመገናኘት የማይደረግ ጥረት የማይፈነቀል ድንጋይ የማይቧጠጥ ዳገት የለም። እንደሚታወቀው የታቦት ንግስ ቀን ድግስ በየቦታው ይኖራል።ካህናትም ይጠራሉ ይባርካሉ ይበላሉ ይጠጣሉ።አንድ ቅዳሜ ቀን በዋለ ንግስ እለት የእነአለቃም የካህናት ቡድን ከቀትር በኋላ ወደእነማዘንጊያ ቤት ተጉዞ ሲበሉ ሲጠጡ ሲጫወቱ ውለው አመሻሹ ላይ ድንግላዊው መነኩሴ ገብረ ሃና መጠጥ አዳክሟቸው ኖሮ ካህናት ጓደኞቻቸው እና የማዘንጊያሽ ቤተሰብ ይስማሙና አለቃ እዚያው እንዲያድሩ ትተዋቸው ይሄዳሉ። አለቃም አደሩ። አዳራቸው ግን የወትሮው አልነበረም። ከማዘንጊያ ጋር ነበር። ማዘንጊያም እንደጎጃሞች አምባው ተሰበረ እንደነጅበላ ይፈር የነበረ አሉዋ። መነኩሴው ድንግልናቸውን አፈረሱ። በማግስቱ አለቃ አዝነው ወደ ሚያገለግሉበት ቤተ ክርስቲያን ሄደው የደረሰባቸውን ተናገሩ። ካህናቱም ምን ሲደረግ አሉ። አለቃም የእናንተስ ስራ ተገቢ ነው ጓደኛ ጥሎ መሄድ አሉ። አለቃና ማዘንጊያም ተጋቡ።