ንጃመና (N'Djamena፣ ዓረብኛ نجامينا /ኒጃሚና/) የቻድ ዋና ከተማ ነው።

የንጃመና ዋና መንገድ

የሚኖርበት የህዝብ ቁጥር (1997 ዓ.ም.) 721,000 ሆኖ ይገመታል። ከተማው 12°10′ ሰሜን ኬክሮስ እና 14°59′ ምሥራቅ ኬንትሮስ ላይ ተቀምጦ ይገኛል።

ከተማው 'ፎርት-ላሚ' ተብሎ በፈረንሳዊው አዛዥ ኤሚል ዣንቲ1892 ዓ.ም. ተመሠረተ። በ1965 ዓ.ም. ቦታው አፍሪካዊ ስም እንዲኖረው ከቅርቡ መንደር 'ኒጃሚና' የተነሣ ስሙ ንጃመና ሆነ።