ነዓኩቶ ለአብ
የዓፄ ላሊበላ ተከታይ እና የዛግዌ ሥርወ መንግስት የመጨረሻ ንጉሥ የሆኑት ዓፄ ነዓኩቶ ለአብ አሁን በርሳቸው ስም በሚጠራ መንደር አቅራቢያ በሚገኝ ዋሻ ስር ያሰሩት ቤተከርስቲያን ነው። አቀማመጡም ከላሊበላ በስተደቡብ ምስራቅ 6 ኪሎ ሜትር ርቆ ነው። ቤተርክስቲያኑ በመጠን አነስተኛ ሲሆን ከተሰራበት ጀምሮ እስከአሁን ድረስ ከበላዩ ዋሻ ሳይደርቅ በሚፈስ የምንጭ ውሃው ይታወቃል። እንዲሁም ይህን ውሃ ለማጠራቀም የሚረዱ፣ በጊዜ ሂደት የጎደጎዱ ደንጋዮች ከቤተርክስቲያኑ ጥንታዊ የመጻሕፍት፣ መስቀሎችና ሙዳዮች ቅርስ ተርታ ይመደባሉ። በነዓኩቶ ለአብ ዋሻ ውስጥ ሌላው ጎላ ብሎ የሚታየው ንግሥት ዘውዲቱ በ20ኛው ክፍለ ዘመን ያሰሩት ከቀይ ጡብ የተሰራ አነስተኛ ህንጻ ነው።
| ||||
---|---|---|---|---|
ነዓኩቶ ለአብ | ||||
የነዓኩቶ ለዓብ ቤተርክስቲያን የውጭ ገጽታ። | ||||
አገር | ኢትዮጵያ | |||
ዓይነት | የዋሻ ውስጥ ቤተርክስቲያን | |||
አካባቢ** | ላስታ | |||
የቅርስነት ታሪክ | ||||
ቅርሱ የተሰራበት ዘመን | 13ኛው ክፍለዘመን | |||
አደጋ | አይታዎቅም | |||
* የአለበት ቦታ ** የዩ.ኔ.ስ.ኮ. ክልል ክፍፍል |