ሙሉ ስማቸው መጋቤ ምሥጢር ዶ/ር አባ ኅሩይ ኤርምያስ - የቅኔና የትርጓሜ መጻሕፍት መምህር - ዜማና ቅዳሴ ዐዋቂ - አገልግሎታቸውን የጀመሩት ከመ/ፓ/ጠ/ጽ/ቤት ተመድበው በሰሜን ምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት ውስጥ በሚገኘው የአቡነ ተከል ሃይማኖት የትውልድ ቦታ ቦሆነው ጥንታዊው የእቲሳ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ገዳም - ቡልጋ የቅኔ መምህር በመሆን ነው፤ ከ1990 - 2003 ድረስ በአዲስ አበባ በወይብላ ቅድስት ማርያም፣ በላፍቶ ቅዱስ ሚካኤልና በቅዱስ ቂርቆስ አብያተ ክርስቲያናት በዋና ጸሐፊነትና ልዩ ልዩ የአስተዳደር እርከን አገልግለዋል። ይሁን እንጂ ለመንፈሳዊ አገልግሎት ቅድሚያ የሚሰጡ በመሆናቸው በአጽዋማትና በበዓላት ቅኔ በመቀኘት፣ ማኅሌት በመቆም፣ ትምህርተ ወንጌል በመስጠት፣ በተለይ በጾመ ፍልሰታ ጊዜ ውዳሴ ማርያም፣ ቅዳሴ ማርያም፣ ጸሎተ ሃይማኖትና ወንጌል በመተርጎም ሰፊ አገልግሎት እንደሰጡ ባገለገሉባቸው ደብር የሚገኙ ካህናትና መምህራን ይመሰክሩላቸዋል። በኤክስቴንሽን የቲኦሎጂ ትምህርታቸውን በመከታተል የባችለር ዲግሪያቸውን በ1997 ከቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ያገኙ (የማዕረግ ተመራቂ ናቸው) ሲሆን የሁለተኛና ሦስተኛ ዲግሪያቸውን በኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ከጀርመን የሐምቡርግ ዩኒቨርስቲ ይዘዋል። ከ2005 እስከ 2010 ለ5 ዐመት የምዕራብ፣ ምሥራቅና ደቡብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ሆነው አገልግለዋል። አሁንም እዚያው ጀርመን የካስል መድኃኔዓለምንና የሐምቡርግ ኪዳነ ምሕረትን አብያተ ክርስቲያናት በማስተዳደር ላይ ሲሆኑ የምርምር ሥራቸውን ጎን ለጎን በማካሄድ ላይ ይገኛሉ። በእቲሳ እያሉ እንደጻፏቸው ከሚነገሩላቸው ከ15 ጊዜ በላይ ተደጋግመው ከታተሙት ከመዝገበ ታሪክ ቁጥር 1 እና 2 ጀምሮ እስካሁን ከ18 በላይ መጻህፍትንና በርካታ የምርምር ሥራዎችን አሳትመዋል። በመጽሄት፣ በጋዜጣና በኢንተርኔት ገጾች የወጡ በርካታ ጽሑፎችም አሏቸው።የኢትዮጵያን ብርቅዬ የስነ ጽሑፍ ውጤቶች በእንግሊዝኛና በጀርመንኛ በመተርጎም የኢትዮጵያን ታሪክና ባህል በማስተዋወቅ ጉልህ አስተዋጽኦ በማበርከትም ላይ ናቸው።

ከመጻሕፍቶቻቸው መካከል

  1. መዝገበ ታሪክ ቁጥር 1
  2. መዝገበ ታሪክ ቁጥር 2
  3. መልካም ዜጋ ማነው?
  4. ገድለ ቂርቆስ - ትርጉም
  5. ገድለ ፋሲለደስ - ትርጉም
  6. ገድለ አቡነ ቀውስጦስ - ትርጉም
  7. ገድለ አቡነ ታዴዎስ - ትርጉም
  8. ገድለ አቡነ አፍጼ - ትርጉም
  9. መጻሕፍትን መርምሩ
  10. መርኆ ምሥጢር
  11. መጽሐፈ ምሥጢር ዘአባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ- ትርጉም
  12. ቅዳሴ ወቁርባን
  13. ቅዱስ ላሊበላ - መንፈሳዊ ቲአትር
  14. ቅድስ አርሴማ - መንፈሳዊ ቲአትር
  15. ኢትዮጵያ የወርቅ ሙዳይ - የግጥም መድበል
  16. መዐዛ ቅዳሴ - ንባቡና ትርጓሜው - አንድምታ
  17. ድርሳን ዘሄርማን - ንባቡና ትርጓሜው - አንድምታ
  18. Review of Comparative classification of Geʿez verbs in the three traditional schools of the Ethiopian Orthodox Church by Muluken Andualem Siferew, published in Aethiopica: International Journal of Ethiopian and Eritrean Studies), 2017
  19. The Issues of ʾAggabāb (Classic Gəʽəz Grammar) According to the tradition of Qǝne Schools, Digital Publication. Digital Library of Hamburg University, 302 Pages, 2019
  20. Nägasi Gǝdäy, Ṭomarä Mäwati, ‘Letter of the dead’ Journal Review, Aethiopica- Uni. Hamburg, 2020.
  21. The Amharic proverbs and their use in Gəʽəz Qəne, in press, AJHC, 2020
  22. ʾAggabab according to the Qane School Tradition, Classical Geez (updated version of ‘The Issues …’), Gorgias Publisher, 384 pages, New York, 2021
  23. The vita of St. Qawǝsṭos a fourteenth century Ethiopian saint and martyr (a new-critical edition, translation, and commentary), Digital publication, Digital Library of Uni. Hamburg, 2014 updated 2021.
  24. Accounts Regarding Historical Events Exposed in the Hagiography of St. Qawǝsṭos, in Jaalhc, 2021
  25. Bitu of Ethiopia and his Heresy, in Jaalch volume 11, Issue 1 (08-2022)
  26. Christologie - nach dem Glauben und der Erklärung der Äthiopisch-Orthodoxen Tewahədo- Kirche, (German) Hamburg, 2022
  27. The place of St. Mary in the Orthodox Christianity of Ethiopia (Journal article)
  28. Certain peculiarities of the liturgical tradition of the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church in comparison with the Coptic Orthodox Church (Journal article)
  29. The Book of Mystery of Abba Giyorgis of Sägla, annotated translation, Nägarit Publisher, May- 2024, Hamburg