ትግራይ ክልል

ትግራይ ሀገር

ትግራይ ከ ኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ሱዳን ትዋሰናለች። ዋና ከተማዋ መቐለ ነው። ሌሎች ታዋቂ ከተሞች ውቅሮ፣ ዛላምበሳ፣ ዓብዪዓዲ ፣ዓድዋ፣ ሑመራ፣ ነበለት፣ ሸራሮ፣ዓዲግራት፣ አኽሱም፣ ሽረ እንዳስላሰ፣ ማይጨው፣ ኮረም፣ ኣላማጣ ናቸው። የሕዝብ ብዛት በ1999 ህዝብ እና ቤት ቆጠራ መሰረት 7.9 ሚልዮን ነው። ትግርኛ የክልሉ ዋና ቋንቋ ነው። እምባ ኣላጀ፣ ፅበት እና ወርሐት በትግራይ ሀገር ያሉ ከፍተኛ ቦታዎች ናቸው። ትግራይ በርካታ ተፈጥሯዊ፣ ባህላዊና ታሪካዊ ሃብቶች የታደለ ሀገር ነው። የ3000 ዓመት የሓ ጥንታዊ ቤተ መቅደስ፣ የ2000 ዓመት የአክሱም ጥንታዊ ሃውልቶች፣ከ4ኛው እስከ 15ኛው ክ/ዘመን እንደተሰሩ የሚታወቀው ከ120 በላይ የሚሆኑ ከኣለት ድንጋይ ተፈልፍለው የተሰሩ ውቅር ኣብያተክርስትያናትና ገዳማት እንዲሁም ሌሌች በርካታ ታሪካዊና ኣርኪኦሎጂካዊ ስፍራዎች የሚገኙበት ሀገር ነው። ትግራይን በባህልና በታሪካዊ ኣመጣጥ ከኤርትራ ነጥሎ ማየት ኣይቻለም። የዳኣማትና የአክሱም ግእዛዊ ሥልጣኔ ባለቤት ናት። ዓድዋ

ትግራይ
ሀገር
Tigray in Ethiopia.svg
የትግራይ ሀገርን በቀይ የሚያሳይ የኢትዮጵያ ካርታ
Flag of the Tigray Region.svg
አገር ትግራይ
ርዕሰ ከተማ መቐለ
የቦታ ስፋት
   • አጠቃላይ 50,286[1]
የሕዝብ ብዛት
   • አጠቃላይ 9,201,000[1]
  1. ^ "፳፻፬ ዓ.ም. የትግራይ ብሔራዊ ስታቲስቲክስ". የትግራይ ማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ. Archived from the original on 2015-09-23. በሰኔ ፳፪ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. የተወሰደ.