የዕለታት ፍቺና  ሥርወ  ቃላቸው

ለማስተካከል
ግእዝ    አማርኛ ፍቺ
እሑድ እሑድ አሐደ- አንድ አደረገ፡፡
ሰኞ  ሰኞ አንደኛኛ- ሁለት ሆነ፡፡ ሁለተኛ ቀን፡፡
ማክሰኞ ማክሰኞ   ሠለሰ- ሦስተ አደረገ፡፡
ረቡዕ ሮብ ረብዕ- አራት አደረገ፡፡ አራተኛ ቀን፡፡
ሐሙስ    አሙስ ኀመስ- አምስት አደረገ፡፡ አምስተኛ ቀን፡፡
ዐርብ ዐርብ ዐርበ- ገባ፣ መሸ፡፡ የሥራ ወይም የምግብ መካተቻ/ የሰንብት መግቢያ/ዋዜማ፡፡
ቀዳሚት ቅዳሜ ቀደመ- ቀደመ፡፡ የመጀመሪያው ሰንበት፡፡

የአውርኀ ፍቺና ሥርወ ቃላቸው

ለማስተካከል
ግእዝ  አማርኛ    ፍቺ
መስከረም መስከረም ዘከረረ- አሰበ፡፡ መዘክረዓም፣ ዓመቱ ማስታወሻ፣ የዘመን መለወጫ፡፡
ጥቅምት ጥቅምት  ጠቀመ - ጠቀመ::
ኅዳር ኅዳር  ኀደረ- አደረ፡፡ የአዝመራ ወር ፣ ገበሬዎች ዱር የሚያድሩበት፡፡
ታኅሣሥ  ተሣሥ   ኀሠሠ- ፈለገ፣ የፍለጋ፣ የፍላጎት ወር፣ አዝመራ የሚሰበሰብበት/ምርት  የሚፈለግበት፡፡
ጥር ጥር ጠረየ- ሰበሰበ፡፡ ጥሪት/ሀብት የሚሰበሰብበት፣ የድካም ዋጋ የሚገኝበት፡፡
የካቲት   የካቲት   ከተ-ከተተ፡፡ የአዝመራ መካተቻ፣ ወደ ጎተራ የሚከተትበት፡፡
መጋቢት መጋቢት መገበ- በቁሙ፡፡ የምትመግበ ወር፣ የጸደይ ወር መግቢያ::
ሚዐዚያ ሚያዝያ  ምዐዝ-ሸተተ፡፡ የበልግ ቡቃያ የሚያብብበት፣የሚሸትበት፣ዘመነ ጸደይ ”መዐዛየ” እንደ ማለት ነው፡፡
ግንቦት ግንቦት ገነበ- ገነባ፡፡ ገቦክረምት፣ የክረምት ጥግ ማለት ነው፡፡
ሠኔ ሰኔ   ሠነየ- አማረ፡፡ ያማረ/መልካም ወር፣ የዘር ወቅት የክረምት መግቢያ፡፡ ቡቃያው የሚያምርበት ፣ በሰላው የሚሸትበት ማለት ነው፡፡
ሐምሌ ሐምሌ ሐመለ-ለመለመ፡፡ የልምላሜ ወር፣ ጎመን የሚበላበት ፣ ልምላሜ የሚታይበት፡፡
ነሐሴ ነሐሴ ነሐሰ-ሠራ፣ ገነባ፡፡ የሥራ ወር፣ ሥራ የሚደራረብበት ማለት ነው፡፡
ጳጉሜ/ን ቋጉሜ  ተረፍ፣ ትርፍ(ቀሪ) ማለት ነው፡፡ ከጽርዕ/ግሪክ ተወረሰ ቃል ነው፡፡