ብርብራ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኝ ተክል ነው።

የተክሉ ሳይንሳዊ ጸባይ

ለማስተካከል

አስተዳደግ

ለማስተካከል

እስከ 12-15 ሜትር ድረስ በቶሎ የሚበቅል ዛፍ ነው።

በብዛት የሚገኝበት መልክዓ ምድር

ለማስተካከል

በጫካ ዳር በሰፊ በኢትዮጵያ ይገኛል።

የተክሉ ጥቅም

ለማስተካከል

መልካም የማጌጫ ዛፍ ነው።

አሣ መርዝ መሆኑ በሰፊ ይታወቃል። ልጡና የበሰለው ፍሬ ከነዘሮቹ እንደ ዱቄት ተደቅቀው በውሃው ላይ ይበተናል። አሣው ተደንዝዞ ወደ ላይ ሲመጣ ማጥመድ ቀላል ይሆናል።[1]

በሌላ ጥናት ዘንድ፣ የብርብራ ፍሬ ለጥፍ በቅቤ ለሙጃሌ ይለጠፋል። የፍሬውም ዱቄት በማርአሚባ በሽታ ይጠጣል። የቅጠሉ ወይም የአገዳው ጭማዊ ጠብታ በጆሮ ውስጥ ለጆሮ ልክፈት ያክማል። የቅጠሉም ለጥፍ ለጥፍረ መጥምጥ ይለጠፋል።[2]

  1. ^ አማረ ጌታሁን - SOME COMMON MEDICINAL AND POISONOUS PLANTS USED IN ETHIOPIAN FOLK MEDICINE Archived ጁላይ 31, 2017 at the Wayback Machine March 1976 እ.ኤ.አ.
  2. ^ የዘጌ ልሳነ ምድር ባህላዊ መድሃኒት ጥናት 1999 ዓም ከጥላሁን ተክለሃይማኖት፣ ሚሩጸ ጊዳይ፣ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ