ቤተክርስቲያን ሦስት ትርጉም ያለው በዘርፍና በባለቤትነት የተጠቃለለ ስም ነው፡፡

  • አንደኛው ትርጉም ፡- የክርስቲያን ቤት የክርስቲያን መሰብሰቢያ የክርስቲያን መገኛ ማለት ነው፡፡ ይህም ማለት ክርስቲያኖች የሚጸልዩበት ሥጋ እና ደሙን የሚቀበሉበት የሚሰግዱበት ከእግዚአብሔር ጋር የሚገናኙበት የጸሎት ቤት ማለት ነው፡፡ (ኢሳ. 56፡7፤ ኤር. 6፡10-16፤ ማቴ. 21፡13፤ ማር. 11፡17፤ ሉቃ. 19፡46 )
ቤተክርስቲያን
  • ሁለተኛ ትርጉም ፡- የክርስቲያን ወገን ክርስቲያን ሁሉ የሚጠራበት ስም ነው፡፡ ‹‹ ቤተ እስራኤል፣ ቤተ ያዕቆብ፣ ቤተ አሮን በማለት የሚጠሩት፡፡ (መዝ. 117፡3፤ ማቴ. 16፡18)
  • ሦስተኛ ትርጉም ፡- ቤተክርስቲያን ሲል ምዕመናን ነው፡፡ ይህም ማለት ቤተክርስቲያን ከክርስቶስ የተገኘ እንደሆነ ነው፡፡ የክርስቲያን ወገኖች ቤተመቅደስ ማለት ነው፡፡ የእያንዳንዱ የክርስቲያኖችን ሰውነት የሚያመላክት ነው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹የእግዚአብሔር ቤተመቅደስ እንደሆናችሁ አታውቁምን›› 1ኛ ቆሮ. 3፡101
 ደሳለሲሳይ