ባቲ ድል ወምበሬ
ባቲ ድል ወምበሬ (1543 - 1552) የአዳል ገዢ እንዲሁም የዘይላ አስተዳዳሪ የነበረው ኢማም ማህፉዝ ልጅ የነበረች ሲሆን አባቷ ከሞተ በኋላ ግራኝ አህመድን አግብታ በባሏ ዘመቻ ሁሉ ተሳታፊ የነበረች ሴት ናት። ግራኝ ከተገደለ በኋላ የእህቱ ልጅ የነበረውን ኑር ኢብን ሙጃሂድ በማግባት የባሏን ሞት የተበቀለች የአዳል መሪ ናት። ባቲ የሚለው ቃል ማዕረጓን ሲያሳይ፣ «ድል ወምበሬ» የሚለው ስያሜ ደግሞ በአማርኛ «የብዙ ድል ባለቤት ነኝ» የሚል ሃሳብ በጠላቶቿ ላይ ለማስረፍ የተጠቀመችበት ነበር። ሁለት ልጆቹዋን፣ ሙሃመድ (1531) እና አህመድ (1533) የወለደቻቸው ግራኝን ተከትላ ዘመቻ በሚያደርጉበት በትግራይ ነበር። በ1543 ባሏ ሲሞትና ልጇ መሃመድም በምርኮ ሲያዝ እርሷ ግን በመጀመሪያ ወደ ሰሜናዊ ምዕራብ ጣና በማምለጥ ኋላ ሐረር ለመግባት ችላለች። የሷ ልጅ እንደተማረከ ሁሉ፣ የአጼ ገላውዲወስን ወንድም ሚናስን ማርካ ስለነበር በሚናስ ምትክ ልጇን ለማስመለስ ችላለች።
የባሏን ሞት ለመበቀል ያሰበችው ድል ወምበሬ ከባሏ ሽንፈትና ሞት 9 አመት በኋላ ኑር ኢብን ሙጃሂድ ( በጊዜው የሐረር ኢምርን) አገባችው። ኢምሩም በኦሮሞ ቡድኖች ሽንፈት የገጠመውን የሐረር ከተማ እንደገና በማነጽና በዙሪያውም እስካሁን ድረስ የሚታየውን የጀጎል ግምብ በማሰራት ሃይሉን አጠናከረ። ከዚያም ወደ መካከለኛው ኢትዮጵያ በመዝመት በ1559 ንጉስ ገላውዲወስን በጦርነት በመግድል የድል ወምበሬን ፍላጎት አሟላ። [1]
ማጣቀሻ
ለማስተካከል- ^ ሪታ ፓንከረስት "Women of Power in Ethiopia Legend and History Archived ኦገስት 8, 2015 at the Wayback Machine"