ቢሻን እንበላለን ቢሻን እንጠጣለን
ቢሻን እንበላለን ቢሻን እንጠጣለን
(39)በሀገራችን እንደተለመደው ድግስ ካለ ቄሱም ሼሁም ሁሉም እንደየሀይማኖቱ ይጠራሉ። አዝማሪዎችም አይቀሩም። ስለዚህ የአለቃ ግዳጅ አንዱ ድግስ መሄድ ነው። ሴትየዋ ያው እንደነገሩ አሸር ባሸር የሆነ ድግስ ብጤ አድርጋ ኖሮ አለቃ ወጡም ቅጥንጥን ጠላውም ውሀ ውሀ ብሎባቸው ኖሯል። ደጋሽ መጥታ አለቃ ይብሉ እንጂ ትላለች። አለቃም «የመጣንበትን ቢሻን እንበላለን ቢሻን እንጠጣለን» ብለው የልባቸውን ተናገሩዋ ድግሱን የፈቀዱ መስለው። /ቢሻን፤ በኦሮምኛ ውሃ ማለት ነው/