በጀት
በጀት ማለት ለወደፊቱ የሚመጣን ገቢና ወጪ የሚተነብይ የንዋይ/ገንዘብ እቅድ ነው። በዚህ እቅድ ውስጥ ቁጠባ፣ ብድር እና ወጪ ይካተታሉ [1]። ግለሰቦች ወይንም ቢዝነሶች ገቢና ወጪያቸው ሲመረመር ከሞላ ጎደል ቋሚ ሆኖ ስለሚገኝ የበጀት ጥቅም ከዚህ ይመነጫል። ማለት፣ ቋሚ ገቢ ወጪ፣ ለወደፊት ይሚሆነን ለመተንበይ አመቺ ነው። ተንብዮ በበጀት መመራት ግለሰቦብ በገንዘባቸው/ንዋያቸው ላይ ሙሉ ቁጥጥር እንዲኖራቸው ያደርጋል። አላስፈላጊ ወጭወችን ለመለየት እና በአቅም መኖርን ለማወቅ ይረዳል።
የበጀት አሰራር
ለማስተካከልቅድሚያ መሰረት
ለማስተካከልበጀት ምሳሌ | |||
---|---|---|---|
የወር ገቢ | |||
የተተነበየ | ተጨባጭ | ልዩነት | |
ደመወዝ - ከስራ ፩ | 200 | 185 | -15 |
ደመወዝ - ከስራ ፪ | 400 | 410 | +10 |
ሌሎች የገቢ ምንጮች | 60 | 50 | -10 |
የወሩ አጠቃላይ ገቢ | 660 | 645 | -15 |
የወር ወጪ | |||
የተተነበየ | ተጨባጭ | ልዩነት | |
ሞርጌጅ/ኪራይ | 300 | 300 | 0 |
መኪና ኢንሹራንስ | 50 | 50 | 0 |
ክሬዲት ካርድ | 50 | 60 | +10 |
ሴቪንግ አካውንት | 50 | 50 | 0 |
ምግብ | 100 | 90 | -10 |
የወሩ አጠቃላይ ወጪ | 550 | 550 | 0 |
በመጀመሪያ ደረጃ ላለፉት ሁለት ወራት የነበረን የወጪ ዓይነቶች ማወቅ ያስፈልጋል። እማይታወቅ ከሆነ ከአሁኑ በመጀመር ለሁለት ወራት መመዝገብ መልካም ልማድ ነው።
ለአንድ ወር እያንዳንዷን ወጪ ከላይ በተቀመጠው የበጀት ዓይነት መሰርት መመዝገብ ጥሩ ምክር ነው።
የወር ደሞዝን ወይንም ሌላ አይነት ገቢን ለብቻው ማስላት፣ ሁለተኛው የበጀት አሰራር ደረጃ ነው።
ከዚያ በኋላ፣ ወጪን ከገበሚ መቀነስና ውጤቱ ነጌቲቭ ከሆነ ያለ አቅም መኖርን ስለሚያመላክት ለወደፊት ይህ እንዳይሆን የወጪ ልማድን እንዴት ማስተካከል እንዳለብን ዘዴ መዘየድ።
ውጤቱ ፖዚቲቭ ሆኖ ከተገኘ ግን ያለ ገቢ ከወጪ ስለሚበልጥ ተራፊውን ገንዘብ በየወሩ ወደ ሴቪንግ አካውንት ማስተላለፍ ጥሩ ተግባር ነው።
ድህረ በጀት
ለማስተካከልበየወሩ በጀቱ መጻፍና መመርመር ይኖርበታል ማለት ነው። ለየጊዜው እንዲስማማ ተደርጎ መሻሻልና መታደስም ይኖርበታል። ወጭና ገቢ በሂደት በሚገባ ከታወቀ በኋላ የወደፊቱን ማቀድ ቀላል ይሆናል። ወጪን ለመቀነስ ወጭን በዝርዝር ጽፎ በዚያ ዝርዝር መሰረት መመራት ከአላስፈላጊ ወጪ ያድናል።
ዕዳና በጀት
ለማስተካከልየበጀት ዋናው ጥቅም አንድ ግለሰብ በራሱ ገቢና ወጪ ላይ ሙሉ ቁጥጥር እንዲኖረው ማስቻሉ ነው። ስለሆነም ግለሰቦች ዕዳ ውስጥ መግባት ሲጀምሩ በቶሎ እንዲያውቁ ይሆናሉ። ስለሆነም ችግሩ ከመባባሱ በፊት አስቀድመው እርምጃ ለመውሰድ ይችላሉ።
አንድ ግለሰብ ዕዳ ውስጥ እየገባ መሆኑን መረዳት ሲጀመር መጀመሪያውኑ የዕዳውን አይነት መለየት አስፈላጊ ነው። ቅድሚያ ትኩረት አግኝተው መከፈል ያለባቸው እማይለወጡ ዕዳወች (ምሳሌ ሞርጌጅ፣ የቤት ኪራይ ..) እና ቀስ ብለው ሊከፍሉ የሚችሉ ተለዋዋጭ ዕዳዎች (ምግብ፣ የኤሌክትሪክ፣ ውሃ ና ሌሎች በጥንቃቄ ሊቀነሱ የሚችሉ ቢሎች) ተለየተው ሊታወቁ ይገባል።
ዕዳዎቹ ከተለዩ በሗላ፣ ዕዳዎቹን ለማስወገድ መንገድ ማበጀት ተገቢ ነው። ለዚህ ተግባር እንዲረዳ «በደህና ጊዜ» በትንሽ በትንሹ ማጠራቀም ጥሩ ነው። ነገር ግን ይህ ተደርጎ ካልሆነ፣ ቀሪ እዳን ቀስ በቀስ ለመክፍል የሚያስችል ስምምነት ከዕዳ-ሰጪው ጋር መግባት ጥሩ ነው። ባንኮች የአንድ ግለሰብ ዕዳ ባለቤት ከሆኑ፣ ግለሰቡን ለመርዳት ፍላጎት ይኖራቸዋል፣ ምክንያቱም ከርሱ ነውና ገንዘብ የሚያገኙት። ለዚህ ተግባር እንዲረዳ ኮንሶሊዴሽን (ሁሉን ዕዳን በአንድ ላይ መሰብሰብ) እና ሪፋይናንሲንግ (ብድርን፣ በተራዘመ ጊዜ እንዲከፍሉ ማስቻል) የሚባሉ ሁለት መሳሪያወችን ባንኮች ይጠቀማሉ። እኒህን ማግኘት እዳ ከቁጥጥር ውጭ እንዳይወጣ ይረዳሉ። ሆኖም እኒህ እድሎች ካልተገኙ ዴቢት ስፔሻሊስት የተሰኙ መካሪዎችን ማነጋገር ይቻላል።
ማጣቀሻ
ለማስተካከል- ^ Sullivan, Arthur; Steven M. Sheffrin (2003). Economics: Principles in action. Upper Saddle River, New Jersey 07458: Prentice Hall. pp. 502. ISBN 0-13-063085-3. https://www.savvas.com/index.cfm?locator=PSZu4y&PMDbSiteId=2781&PMDbSolutionId=6724&PMDbSubSolutionId=&PMDbCategoryId=815&PMDbSubCategoryId=24843&PMDbSubjectAreaId=&PMDbProgramId=23061. Archived ዲሴምበር 20, 2016 at the Wayback Machine "Archive copy". Archived from the original on 2016-12-20. በ2021-02-24 የተወሰደ.