በርኒ ሳንደርስ
የአሜሪካ ፖለቲከኛ
በርናርድ "በርኒ" ሳንደርስ (ተወለደ በእ.ኤ.አ. ሴፕቴምበር 8 1941) አሜሪካዊ ፖለቲከኛ እና የቬርሞንት ጁኒየር ሴናተር ነው። ለእ.ኤ.አ 2016ቱ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንታዊ ምርጫ የዴሞክራቲክ ፓርቲን በመወከል የሚወዳደር እጩ ነበር። ከእ.ኤ.አ. 2015 ጀምሮ ዴሞክራት የሆነው በርኒ ሳንደርስ ፥ በአሜሪካ ኮንግረስ ታሪክ ውስጥ ለረጅም ጊዜ ያገለለ ግላዊ ፖለቲከኛ ነው። ከዴሞክራቶች ጋር ኅብረት ማድረጉ በኮሚቴ ሥራዎች ላይ ሥልጣን እንዲኖረው አድርጎ ነበር ፤ ይህም አንዳንዴ ዴሞክራቶችን አብላጫነት ሰጥቶአቸዋል። ሳንደርስ በእ.ኤ.አ. ጃኑዋሪ 2015 ላይ በሴኔት በጀት ኮሜቴ ውስጥ ራንኪንግ ማይኖሪቲ ሜምበር ሆነ ፤ ከዚያ በፊት የሴኔት የቀድሞ ወታደሮች ጉዳይ ኮሚቴ ውስጥ ሊቀ-መንበር በመሆን ለሁለት ዓመታት አገልግሏል። ራሱን ዴሞክራሲያዊ ሶሻሊስት ብሎ የሚጠራው በርኒ ሳንደርስ የሠራተኞችን መብት እና የኢኮኖሚያዊ እኩልነትን በጽኑ ይደግፋል።
በርኒ ሳንደርስ | |
---|---|
የበርኒ ሳንደርስ ኦፊሲዬላዊ የሴኔት ፎቶግራፍ - እ.ኤ.አ. 2007 | |
ባለቤት | ዲቦራ ሺሊንግ (ከእ.ኤ.አ. 1964 - 66) ጄን ኦሜራ (ከእ.ኤ.አ. 1988 ጀምሮ) |
ሙሉ ስም | በርናርድ ሳንደርስ |
የትውልድ ቦታ | ብሩክሊን ኒው ዮርክ ከተማ ዩ.ኤስ. |
የልደት ቀን | እ.ኤ.አ. ሴፕቴምበር 8 1941 |
ፊርማ |
ሳንደርስ ተወልዶ ያደገው ብሩክሊን ኒው ዮርክ ከተማ ውስጥ ሲሆን የተመረቀው ደግሞ በእ.ኤ.አ. 1964 ከሺካጎ ዩኒቨርስቲ ነበር።