በማስተዋል ወደ ባለጠኘት ማደግ

መግቢያ ለማስተካከል

በማስተዋል ወደ ባለጠግነት ማደግ የተባለው መጽሐፍ Think and Grow Rich ከሚባለው የናፖሊዮን ሒል ድንቅ መጽሐፍ ወደ አማርኛ የተተረጎመ ነው። የተትረፈረፈ ሀብት የሚስገኙ፣ ፍቱን የሆኑ ድንቅ ምስጥሮችን የያዘው ይህ መጽሐፍ ታዋቂው ናፖሊዮን ሂል ፅፎት ደራሲና ኢንጂነሩ የወርቁ ልጅ ሐይሉ ወደ አማርኛ በ2000 ዓ.ም መለሰው። የታዋቂው ቱጃር አንድሪው ካርኒጌ፤ በታሪክ ተፈትነው የተረጋገጡ አሥራ ሦስቱ ባለጠጋ የመሆኛ ቀመሮችና ሚሰጥሮቻቸውን ይዞ፤ ከ500 በላይ በሚሆኑ ታወቂ አሜሪካዊያን ሀብታሞች ላይ የሀያ አምስት ዓመት ጥልቅ ጥናት ተደርጎበት፤ በዓለም ያሉ የሰው ዘሮችን ሁሉ ከድህነት ለማላቀቅና ወደ ባለጠግነት እንዲመጡ ለማድረግ ታስቦ የተፃፈ ድንቅ መጽሐፍ፡፡ ከተፃፈበት ከ1950 ጀምሮ ላለፉት 50 ዓመታት ተወዳጅነቱን ጠብቆ የኖረ መጽሀፍ! ዛሬ ደግሞ በአሜሪካና በአውሮፓ የታየውን እድገት በናፍቆት በሚጠብቁ ኢትዮጵያዊያን ዘንድ እንዲነበብ ወደ አማርኛ ተተርጉሟል፡፡

ሁለተኛውን ዕትም በ2008 ዓ.ም የታተመ ሲሆን፣ ሦስተኛው ዕትም ማስተካከያና እርምት ተደርጎበት በ2014 ዓም ለህትመት በቅቷል።